በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም በዓሉ በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 20/20003 ዓ.ም፤ ሰፕቴምበር 30/20010)፦ ዓመታዊው የእመቤታችን የቅ/ድንግል ማርያም በዓለ ንግሥ በግሸን ደብረ ከርቤ በደመቀ ሁኔታ በመከበር ላይ እንደሆነ ተባባሪ ደጀ ሰላማውያን ከሥፍራው ዘግበዋል። ከ1000 በላይ ቁጥር ባላቸው መኪናዎች፣ በእግር እና በከብት ጀርባ ተጭኖ የመጣው ቁጥሩ በብዙ ሺዎች የሚቆጠረው ኦርቶዶክሳዊ ምእመን ሰሞኑን ጀምሮ በቦታው የከተመ ሲሆን በዓሉን ካከበረ በሁዋላ ወደየአካባቢወው ተመልሶ ለመሔድ እስከ መስከረም 23 ቀን ድረስ እንደሚቆይ ተዘግቧል።
የደብረ ግሸንን ታሪክ እና በዓሉን በተመለከተ አጭር ዘገባ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩት በሊቁ በመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ድምጽ (http://deje-selam-mezmur.blogspot.com/2010/09/blog-post_30.html) ያዳምጡ/ ይመልከቱ።
