ወያኔ ወደ ጎሬቤት አገር ለሺያጭ ሊያቀርብ ያሰበውን መብራት ጁቡቲ ላይ ሊጀምር እንደሆነ ተገለጸ
ህዝባችን በሳምንት 3 ግዜ ብቻ መብራት በሚያገኝባት ሀገር የአገሪቱ መብራት ሃይል ኩባንያ ለጅቡቲ መንግስት እስከ 200 ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመሸጥ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ።
በኢትዮጵያው ሚሊኒየም አከባበር ሥነሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከአሁን ቦኋላ ሻማ የሚያበራው ለልዴት ቀን ብቻ ይሆናል ተብሎ በመለስ ዜናዊ የተለመደው የውሽት ተስፋ ቃል የተገባ ቢሆንም ችግሩ እስከዛሬ ተባብሶ እንደቀጠለ ይታወቃል።
በመላው አገሪቱ ያለው ከፍተኛ የሆነ የመብራት ሃይል እጥረት ህዝባችንን ለከፍተኛ እሮሮ እየዳረገው ባለበት በአሁኑ ሰዓት፤ ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ መብራት ለጎሬቤት አገር አሳልፎ በውጪ ምንዛሪ ለመሸጥ እያደረገ ያለው መሯሯጥ የስልጣን ዕድሜው እንደማይረዝም በመገመት የተገኘውን ገንዘብ ዘርፎ ለመሄድ እንዲያስችለው ታስቦ እንደሆነ የወያኔን ባህሪ የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
ወያኔ ወደጁቡቲ ለመሸጥ እየሰራ ካለው የመብራት ሃይል በኪሎዋት 70 ዶላር ገንዘብ እንደሚያገኝ ስምምነት ላይ መደረሱ የተገኘው መረጃ ያረጋግጣል። የአገሪቱ ዜጎች ከተወለዱበትና ከአያት ቅድሜ አያቶቻቸው ጀምረው ከሚኖሩበት ቀያቸው እየተፈናቀሉ ለአረብና ለ ኤሽያ ቱጃሮች እየተቸበቸበ ካለው ድንግል መሬታችን ሽያጭ እስከዛሬ ምን ያህል ገንዘብ እንደተገኘ በውል የማይገለጸውና ምን ሥራ እየተሰራበት መሆኑ የማይታወቀው ገንዘቡ በአብዛኛው ውጪ አገር በሚገኙ ባንኮች በግለሰብ ሥም ስለሚቀመጡ ነው ተብሎአል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ የሚያካህደውን የሃብት ዘረፋና የአገር ክህዴት ወንጀል ለማስቆም ጠንክሮ መታገል እንደሚኖርበት የግንቦት 7 ድምጽ በተደጋጋሚ ሲዘግብ እንደቆየ ይታወሳል።