የኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የIMF ዘገባ

ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት በእንግሊዘኛ ምህፃሩ IMF ባላፈው ሳምንት ባወጣው የዓለምን የኢኮኖሚ እድገት በዳሰሰበት ዘገባ እጎ.አ በ 2010 የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ በ 7.5 በመቶ ማደጉን አስታወቀ። ይሁንና በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ 2011 ዓ.ም ወደ 40 በመቶ በደረሰው የዋጋ ግሽበት ሳቢያ የዘንድሮው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት እንደሚቀንስ የድርጅቱ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል ። በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥት የሚሰጠውን ብድር ማቆምንና ፣ የወለድ መጠን እንዲጨምር ማድረግን የመሳሰሉ እርምጃዎች መወሰድ እንደሚገባቸው ኃላፊው አስታውቀዋል ። ያነጋገራቸው የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል። ያዳምጡ