ከዲፕሎማ በላይ የሚማሩ የኢሕአዴግ አባላት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ታዘዙ
የምርጫ 97 ዓይነት እንቅስቃሴ ታይቷል በሚል ጥብቅ ግምገማ እየተካሄደ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በ119 ወረዳዎችና አሥሩም ክፍላተ ከተማዎች ውስጥ የሚገኙና ከዲፕሎማ በላይ በመማር ላይ የሚገኙ የኢሕአዴግ አባላት፣ እስከ 2005 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ትዕዛዝ መተላለፉን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡