ድርጅቶች ቪሳት ማስገባት የሚያስችላቸው መመርያ ወጣ

የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንቅሰቃሴያቸው በአብዛኛው በኢንተርኔት ላይ የተመረኮዘ ኩባንያዎችና ድርጅቶች፣ ቪሳት የተባለውን በሳተላይት አማካይነት የኢንተርኔትና የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን መሣርያ ማስገባት የሚያስችላቸውን መመርያ ማውጣቱን አስታወቀ፡፡