የኢትዮጵያ ሙዚቃ ዕንቁ – አስናቀች ወርቁ

የክራሯ ንግሥት አስናቀች ወርቁ, Asnakech Workuገነት አየለ ከፓሪስ – ፈረንሣይ

በቅርቡ ከዚህ ዓለም የተለየችንን የክራሯ ንግሥት አስናቀች ወርቁን አስመልክቶ በሥራ እና በማኅበራዊ ግንኙነት ከሚያውቋት ሰዎች አንዷ ፀሐፊና ጋዜጠኛ ገነት አየለ ነች። ይህንን የተረዳው የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ፤ “ስለአስናቀች የምትው አይጠፋምና እባክሽን!” የሚል መልዕክት ለገነት አየለ አስተላልፎላታል። ጋዜጠኛ ገነትም ሳትውልና ሳታድር ስለአስናቀች የምታውቀውን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ አንባብያን አቋድሳለች።