መለስ፣ ሲአይኤ እና ኢትዮጵያ – ክፍል 3 (የመጨረሻ)

ፖል፦ ከኢቫንጀሊካን ቤተሰብ እንደወጣህ ተነግሮኛል እውነት ነው?

መለስ፦ የለም። ወላጆቼ ኦርቶዶክስ ነበሩ። ትግራይ ውስጥ ጥቂት የኢቫንጀሊካል ቤተሰብ ነው ያለን። በኤርትራ ውስጥ ካሉ ፕሮቴስታንቶች በጅጉ ያነሱ ናቸው። ትግራይ ውስጥ ያሉ ፕሮቴስታንቶች ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይን ይደግፋሉ። ግን ፕሮቴስታንቶች የኤርትራ ነጻ አውጭ ግንባር ውስጥ አስፈላጊ የሆኑትን ያህል በወያኔ ውስጥ አስፈላጊ አይደሉም።