ጥሪው የማህጸን፤ ምላሹም የዕትብት ሐዲድነት ነበር
ለልጅ ተክሌ የተሰጠ ምላሽ
ሥርጉተ ሥላሴ
አረሙ ወያኔ በየትኛውም መስፈርት ኢትዮጵያዊነትን የመቀማት ሞራሉም ሆነ አቅሙም የለውም – በጣም በእርግጠኝነት!
ጤና ይስጥልኝ ሞገደኛው ተክሌ እንደምን ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? የብዕር አጣጣልህ እንደ አቤ ቶኬቻው ውብ ስለሆነ ለረጅም ጊዜ እያደንኩ አነባለሁ። ጠረባህንም አክሎ። በጠረባህ ዙሪያ አንድ ቀን የምለው ይኖረኛል … ዛሬ ግን ልታገሰው ስላልቻልኩት ማለት ፈለግኩ … በሦስት ነገሮች ዙሪያ … እንዲህም እላለሁ … እኔው …