መድረክ የወ/ት ብርቱካንን ጉዳይ ችላ አለማለቱን አስታወቀ
‹‹ኢሕአዴግ በጉልበት አሸንፏል እኛ ደግሞ የሞራል የበላይነት አለን›› አቶ ገብሩ አስራት
(በኃይሌ ሙሉ)
በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳን ለማስፈታት መድረክ የማያቋርጥ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንና ሊቀመንበሩ ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ገለጹ፡፡ ድርጅቱ የወ/ት ብርቱካንን ጉዳይ ችላ እንደማይልም አስታውቀዋል፡፡