የኢሕአዴግ መንግስት 52 ቢሊየን ባለ100 እና 50 ብር ኖቶች ሊያሳትም ነው

ግሽበቱን ያባብሰዋለረ ተብሎ ተሰግቷል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መስከረም 6 ቀን 2004 ዓ.ም. September17, 2011)  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ 52 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አዳዲስ የመቶ እና የሃምሣ ብር ኖቶችን ሊያሳትም መዘጋጀቱ ተሰማ። በሀገሪቱ ታሪክ ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ ታትሞ የማያውቅ ሲሆን ለማሳተም ብቻ ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተገምቷል።