የሽብር ተጠርጣሪዎች እስር አንድነትና መንግሥትን አፋጧል
– ‹‹መንግሥት ድርጊቱን ካላቆመ ዓመፅ ይከሰታል›› አንድነት
– ‹‹በሽብር የሚጠረጠሩትን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይቀጥላል›› መንግሥት
– ‹‹በሽብር የሚጠረጠሩትን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይቀጥላል›› መንግሥት
መንግሥት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችንና አንድ ጋዜጠኛ በሽብር ጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ተከትሎ፣ በመንግሥትና በአንድነት ፓርቲ መካከል መወነጃጀል ተጀምሯል፡፡