የቦምብ ፍንዳታ በሶማሊያ

ዛሬ በማዕከላዊ ሶማሊያ በለድዌይን ከተማ ውስጥ በኣንድ ፖሊስ ጣቢያ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ ከ10 ሰዎች በላይ ተገድለው በርካቶች መቄሰላቸው ተሰማ።

በመኪና ላሊ የተጠመደ ቦምብ መፈንዳቱን ተከትሎ ታጣቂዎችም ተኩስ ከፍተው ለማምለጥ የሞከሩ ፖሊሶችን ሲገድሉ ማየታቸውን የዓይን እማኞች ተናግሯል።