ፓትርያርኩና ዲ/ን በጋሻው: Picture of the Year

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2010)፦ ቅ/ፓትርያርኩ ሰኞ ማታ በተዘጋጀ የራት ግብዣ ላይ “በዓለ ሲመታቸውን ላሳመሩ” ሰዎችና ማህበራት የምስጋና ሰርተፊኬት ሰጥተዋል። ሰርተፊኬቱን ያሰራውና የተሸለመው ራሱ ሐውልቱን ያሰራው የነ ወ/ሮ እጅጋየሁ ኮሚቴ እና የነ ዲ/ን በጋሻው ማህበር የሆነው “የቅ/ማርያም የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ማህበር” የተባለው ነው።  ከሁለት ሳምንት በፊት በአዋሳ ከተማ እንዳያስተምሩ የታገዱት ዲ/ን በጋሻውና የሚመራቸው መዘምራን ከፓትርያርኩ እጅ የተቀበሉት የምስክር ወረቀት የታገደባቸውን ጉባዔ ለማካሄድ አንድ እመርታ ፈጥሮላቸዋል። የታገዱትን ጉባዔ በድጋሚ ለማካሄድ ድርድር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል። ጉባዔውን ያሳገዱት የቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪም በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።