የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲገመገሙ ቦርዱ አለመሳተፉን አስታወቀ
– ‹‹በግምገማው የተዘጋ የትምህርት ተቋም የለም›› የግል ከፍተኛ ተቋማት ቦርድ
የትምህርትን ጥራት ከማረጋገጥ አኳያ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ባደረገው የአንድ ዓመት ግምገማ፣ ኤጀንሲው በሚያቀርባቸው ውይይቶችና ውሳኔዎች ላይ ከመሳተፍ ውጭ፣ በግምገማው ላይ አለመሳተፉን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበር ቦርድ አስታወቀ፡፡