የአርቲስት ደበበ እሸቱ መታሰርና ውዝግቡ

ኢትዮጵያዊዉ እዉቅ ተዋኝና የመድረክ ሰዉ ደበበ እሸቱ በአሸባሪነት ጥርጣሬ መያዙ ወትሮም የተካረረዉን የመንግሥት፥ የተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾችን ዉዝግብ ይበልጥ አንሮታል።

ኢትዮጵያ መንግሥት ደበበ የታሰረዉ ከአሸባሪ ቡድን ግንኙነት እንዳለዉ በመጠርጠሩ ነዉ ባይ ነዉ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የመብት ተሟጋቾች ግን መንግሥት ሰዎችን በአሸባሪነት የሚወነጅለዉና የሚያስረዉ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ለማዳከምና ለማሸማቀቅ ነዉ በማለት ይወቅሳሉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንዘገበዉ ደበበ እሸቱ ከታሰረበት ጊዜ ጀምሮ ባለቤቱ አላዩትም፥ ፍርድ ቤት ሥለመቅረብ አለመቅረቡም የሚታወቅ ነገር የለም።