አርቲስት ደበበ እሸቱ በሽብርተኛነት ክስ ማእከላዊ ታሰረ
በሽብርተኛ ክስ ውብሸት ጥላሁን፣ ርዮት አለሙ እና ሁለት የስዊድን ጋዜጠኞች ክስ ተመስርቶባቸዋል
Ethiopia Zare (አርብ ጷግሜን 4 ቀን 2003 ዓ.ም. September 9, 2011)፦ ታዋቂው የጥበብ ባለሙያና የቅንጅት ለአንድነትና ዲሞክራሲ አመራር አባል እንደነበር የሚታወቀው አርቲስት ደበበ እሸቱ በኢህአዴግ መንግስት “ሽብርተኛ” ተብሎ ከተፈረጀው ግንቦት 7 ንቅናቄ ጋር ግንኙነት አድርጓል በሚል ማእከላዊ እስር ቤት መግባቱ ተገለጸ።