የልኳንዳ ነጋዴዎች በቄራ የቁም ከብት ገበያ አንገበያይም አሉ

የልኳንዳ ነጋዴዎች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቄራ አካባቢ በሚገኘው የቁም ከብት ገበያ ውስጥ ያካሂዱ የነበሩትን የከብት ግዥ ትተው፣ በሌሎች የገበያ ሥፍራዎች ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን፣ አቶ ወልደ ገብርኤል አባተ የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ሊቀመንበር አስታወቁ፡፡