ምነው ልጅ ተክሌ ጥምረትን ጠመዱ – ውህደትን ወደዱ?
አዜብ ጌታቸው
ከጥቂት ቀናት በፊት ልጅ ተክሌ ከካናዳ “ያጣነው ጥምረት አይደለም ድፍረት ነው” በሚል ርዕስ የአፋራ ህዝብ ፓርቲ፣ ግንቦት ሰባት እና የኢትዮጵያ ህዝብ የአንድነትን የፍትህ ንቅናቄ ጥምረት መመስረታቸውን አስመልክተው ያቀረቡልንን ጽሑፍ ያነበብኩት በጽሞና ነው። በርካታ ነጥቦችን የዳሰሰ ማለፊያ ጽሑፍ ነው።
የልጅ ተክሌን ጽሑፍ ሳነብ፤ አንዳንዴ ቁጭትና ምሬታቸው የኔም ቁጭትና ምሬት እየሆነ አብሬያቸው ስመረርና ስቆጭ፤ አንዳንዴ ደግሞ ውህደት እንዴት? ውህደት ማንና ማ? የሚሉትን ጥያቄዎች ችላ ብለው በደፈናው መጣመር ሳይሆን መዋሃድ ነው በማለት የሚሰነዝሩት ሃሳብ የቀጭን ጌታ ቀጭን ትዕዛዝ እስኪመስለኝ በአግራሞት እየቆዘምኩ፤ አልፎ አልፈፎ ደግሞ ፋታ ወሰድ አድርጌ በምሬቶቻቸውና በምኞቶቻቸው መካከል ያሉትን ተጨባጭና ነባራዊ እውነታዎች እያብሰለሰልኩ ነበር የልጅ ተክሌን ጽሁፍ የዘለቅሁት። መብሰልሰሌም ይህችን የዛሬዋን ጽሑፍ ወለደ። … ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!