ኢትዮጵያና ኤርትራ በፀጥታው ምክር ቤት ማዕቀብ ላይ ተፋጠዋል

‹‹ማዕቀቡ የኢትዮጵያ የተናጠል ጉዳይ አይደለም››  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ዳግመኛ ሊጥል ባሰበው ማዕቀብ ምክንያት፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ዲፕሎማቶች ኒውዮርክ ውስጥ እየተወዛገቡ መሆኑ ተሰማ፡፡