ከኃላፊነታቸው የተነሱት የንግድ ባንክ ከፍተኛ አመራር ቢሮ ታሸገ

– አንደኛው አመራር አራት ደረጃ ዝቅ ተደርገው ተመድበዋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ባስተላለፉትና በጻፉት ደብዳቤ ከኃላፊነታቸው ተነስተው የነበሩት አቶ ክፍለ ጽዮን ማሞ የቢሮአቸው ቁልፍ ተቀይሮ መታሸጉን ለሪፖርተር ገለጹ፡፡