ዝዋይ ላይ የሚፈጸመው ተደጋጋሚ ግድያና ዝርፊያ ነዋሪዎችን አስቆጥቷል
– ነዋሪዎች ለአራት ሰዓታት መተላለፊያ መንገድ ዘግተው ነበር
ከአዲስ አበባ በ160 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በስተደቡብ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኘው የዝዋይ ከተማ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና ዝርፊያ ያማረራቸው ነዋሪዎች፣ ሐምሌ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. ለአራት ሰዓታት ያህል መተላለፊያ መንገድ በመዝጋት መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡