ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ‘ማህበረ ቅዱሳን’ ይሆን?
በተመስገን ደሳለኝ
የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት ‹‹ጠንካራ ይዞታ›› የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል፡፡ በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል፡፡ በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) ‹‹ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከ ገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ‹ወንበዴ›ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት›› የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው፡፡