‹‹በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የለበትም›› አቶ ኤርሚያስ አመልጋ
ባለፉት 15 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ባከናወኑት ፈር ቀዳጅ የንግድና የኢንቨስትመንት ክንውኖች ምክንያት፣ ‹‹ኢትዮጵያን አሜሪካን›› በተሰኘው በአሜሪካ ዳያስፖራ ቢዝነስ ኤንድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተሸለሙት፣ የአክሰስ ካፒታል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ የታዳሚውን ቀልብ የሳበ ንግግር አድርገዋል፡፡