“ጊዜ መስተዋቱ!” ተስፋዬ ገ/አብ ማነው?

(ከወልደሚካኤል መሸሻ)

ውድ አንባቢያን ይህን ጽሑፍ ጀምሬ ያጠናቀቅሁት ወደ እ . ኤ. አ በ2012 መጀመሪያ ነው። ለምን እስከአሁን አቆየኸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው ታዲያ። ተገቢ ጥያቄ ነው። የተለያዩ አቅጣጫዎችን የማየትና የማሰላሰል ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ ደግሞ በአነሰኛ መጽሐፍ መልክ ባሳትመውስ የሚል አሳብ እየተደቀነብኝ መጥቶ ነው። ሁለቱም ተራ በተራ ተፈታተኑኝ። የትኛውን እንደምመርጥ ማውጣት ማውረዱን ቀጠልሁ። ጽሑፍን እንድያዩትና አሳባቸውን እንዲሰጡኝ ለጥቂት ወዳጆቼ ላክሁ። አንዳንዶቹ ቶሎ ጽሑፉ እንዲወጣ የሚገፋፋ አሳብ ሰጡኝ። አንዳንዶች ከማስጠበቅ ውጭ ላያልፉ ሆኑ። በዚህ ላይ እያለሁ ለጽሑፉ መሠረት የሆነው የእምዬ ጠላት በመርዘኛ ብዕሩ ብቅ ማለቱን ሰማሁ። ወዳጆቹ ከወዲህ ወዲያ እያሉ መሆኑንም አዳመጥሁ። እርሱም የእምዬ ልጆችን የማባላቱን ሥራ ማጠናቀቁን ከወብሳይቱ ተመለከትሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …