ከአዳዲስ የህንድ ኩባንያዎች የሁለት ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ይጠበቃል
– ኩባንያዎቹ እስከ 500 ሺሕ ሔክታር መሬት ሊጠይቁ ይችላሉ
በዓለማችን ትልቁ የአበባ አምራች በሆነውና በኢትዮጵያ በ100 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ በተለያዩ ግብርና ምርቶች በተሰማራው በካሩቱሪ አስተባባሪነት የተመራው 30 የህንድ ኩባንያዎችን ያቀፈ የንግድ ልዑክ፣ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በሚገመት የአግሮ ቢዝነስ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ዕቅድ እንዳለው፣ የካሩቱሪ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሚስተር ሳይ ራማክሪሽና ካሩቱሪ ለሪፖርተር ገለጹ፡፡