የአንድነት አመራር አባላት ጊዜያዊ እገታ

የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ዓመራር አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ኣበባ ላይ ለጠሩት ሰልፍ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዳልቻሉ ኣስታወቁ በኢትዮፕያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ የፓርቲው ዓመራሮች ዛሬ ለተወሰኑ ሳዓታት በፓሊሶች ታግተው መለቀቃቸውን ፓርቲው ኣስታውቋል ።