ከ230 በላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የንግድ ሰዎች ተመረቁ

– አቶ አባዱላ ገመዳና አቶ አዲሱ ለገሰ ይገኙበታል

ዓለም አቀፍ የአመራር ኢንስቲትዩት ከግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አዲሱ ለገሰን ጨምሮ፣ 236 ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችን፣ የመከላከያ ጄነራሎችንና ታዋቂ የንግድ ሰዎችን በትናንትናው ዕለት አስመረቀ፡፡