ደቡብ ግሎባል ባንክ ሥራ ለመጀመር የባለአክሲዮኖችን ጉባዔ ጠራ

(በጋዜጣው ሪፖርተር)

በምሥረታ ሒደት ላይ የነበረው ደቡብ ግሎባል ባንክ አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ የባንኩን የባለአክሲዮኖች የመጀመሪያ ጉባዔ ለመስከረም 9 ቀን 2003 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ መጥራቱን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ የሕዝብ ግንኙነት አስታወቀ፡፡