የመድረክ ጥሪ የድርድር
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ጋር በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመደራደር ጥሪ አቅርቧል ።
የመድረክ ጥሪ በተግባር እንዲተረጎምም ህዝቡ በገዥው ፓርቲ ላይ በሚቻለው ሁሉ ተፅዕኖ እንዲያያሳድር በመግለጫው ጠይቋል ። ከተቃዋሚዎች ጋር አብሮ እንደሚሰራና ለድርድርም ዝግጁ እንደሆነ ሲገልፅ የቆየው ኢህአዲግ የአሁኑን የመድረክ ጥሪ መቀበል አለመቀበሉን ለመጠየቅ የአዲስ አበባው ወኪላችን ታደሰ ዕንግዳው ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ።