ወቅታዊ የቴሌ-ኮንፍረንስ ስብሰባ ግብዣ – ጋባዥ፥ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የሰሜን አሜሪካ ግብረ ኃይል – ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ዜጎች

ጋባዥ፥ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት የሰሜን አሜሪካ ግብረ ኃይል
ተጋባዥ፥ ኢትዮጵያውያን ሚዲያዎች እና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ዜጎች

በስብሰባው ላይ የሚገኙት እንግዶች፥

1)የተከበሩ አቶ ተክሌ በቀለ – የአንድነት ፓርቲ ትሬዠረር
2)አቶ ሀብታሙ አያሌው – የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ምክትል ሃላፊ
3)የሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ተወካይ

እንደሚታወቀው ላለፉት ሦስት ወራት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ከገዢው ፓርቲ ያጋጠሙትን እንቅፋቶች በሰላም እየተራመደ በጎንደር፣ በደሴ፣ በባህርዳር፣ በአርባ ምንጭ፣ በጅንካ፣ በፍቼ፣ አዳማ ከተሞች ሕዝቡን ያሳተፉ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እና ህዝባዊ ስብሰባዎች አከናውኗል፡፡ አንድነት የጀመረውን ይኽን ሕዝባዊ ሰላማዊ ንቅናቄ የመጀመሪያ ምዕራፍ ከሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች ጋር በመሆን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በሚያካሂደው ህዝባዊ ሰልፍ እንደሚያጠናቅቅ ለመንግስት ቀደም ብሎ አስታውቋል። ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስፈልገው ከ24 ሰአቶች ቀደም ብሎ ለመንግስት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ እንዳልሆነ ህገ-መንግስቱ እንደሚደነግግ ቢታወቅም አንድነት ግን ከነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት እንዲያውቅ በማድረጉ ሰልፉ በታቀደው ቀን መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠኋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ይደረጋል፡፡

ስለዚህ እሁድ መስከረም 5 ቀን 2006 ዓ.ም. (September 15, 2013) በአዲስ አበባ በሚካሄደው የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ሰላማዊ ሰልፍ እና በቀጣዩ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ትግላችን ቀጣይ ምዕራፎች ላይ ከፍ ብለው የተጠቀሱት እንግዶች በቴሌ-ኮንፍረንስ ከኢትዮጵያውያን ጋር አሳብ ስለሚለዋወጡ የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ የሰሜን አሜሪካ የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ ግብረ ኃይል በአክብሮት ጋብዞዎታል።

በዚኽ ቴሌ-ኮንፍረንስ ከተጋበዙት ሚዲያዎች ውስጥ ጥቂቶቹ፥
1) ፓልቶክ ሚዲያዎች፥ ቃሌ፣ ሲቪሊቲ እና ኢትዮጵያዊ ከረንት አፌርስ
2) ሪዲዮ እና ቴሌቪዥን ስርጭቶች፥ የአሜሪካ ድምጽ (አማርኛ፣ ትግሪኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራሞች)፣ ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ፣ የጀርመን ሬዲዮ ጣቢያ፣ የዲሲ እና ሌሎች የኢትዮጵያ ሬዲዮኖች በሰሜን አሜሪካ በሙሉ
3)ድረገጾች፥ ዘሐበሻ፣ ኢትዮሚዲያ፣ ኢትዮሚዲያ ፎረም፣ አቦጊዳ፣ ኢትዮጵያዊ ሪቪው፣ አውራምባ ታይምስ፣ ኢትዮጵያዊ ከረንት አፌርስ ፎረም እና ሌሎች

ቴሌ-ኮንፍረንሱ የሚደረገበት ቀን እና ሰዓት፥

ቀን፥ ቅዳሜ መስከረም 4 ቀን 2006 ዓ.ም. (Saturday, September 14, 2013)
ሰዓት፥ ከቀኑ 1፡00 ሰዓት (1:00 PM Eastern Time)
በቴሌ-ኮንፍረንሱ ለመሳተፍ፥ (267) 507-0240 ይደውሉ እና 20-18-20 ኮድ ይጠቀሙ

የህዝብ ሰላማዊ ትግል ኃይል ከገዢዎቹ ኃይል ሚሊዮን ጊዜ ይበልጣል!1176287_716148551734942_1505200997_n