ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ የአደባባይ ዝርፊያን አካሄደ፣ ከያንዳንዱ የሞባይል ቴሌፎን ተጠቃሚ ሃምሳ ብር ነጠቀ

በሰሜን አፍሪቃ ህዝባዊ አመጽ ከተነሳና በርካታ የአፍሪቃ ሃገራትን ካርበደበደ ወዲህ በያቅጣጫው ውጥረት ውስጥ በመዘፈቁ የሚያደርገውና የሚጨብጠው ጠፍቶት የቆየው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የህዝብን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር በሚል የለቀቀው የአባይ ግድብ ግንባታ ነጠላ ዜማ ሽያጭ የታሰበውን ያህል ሊከናወን ባለመቻሉ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የሞባይል ተጠቃሚ ሃምሳ ብር እንዲቆረጥ ማድረጉን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ። እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እንዲህ ያለውን ግልጽ የሆነ ዘረፋ የፈጸመው በማን አለብኝነትና በጉልበት የኢትዮጵያዊያንን ይሁንታ ሳያገኝና ምንም አይነት መረጃ ሳይሰጥ እንደሆነ ታውቋል።

ዘጋቢያችን ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የፈጸመውን ዝርፊያ አስመልክቶ አስተያየት እንዲሰጡት ጥያቄ ካቀረበላቸው የሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች አንዱ በሰጡት ምላሽ፣ እቅርብ ቀን ሞባይሌን አንድ መቶ ብር ከፍየ ሂሳብ ማስሞላቴን በትክክል አውቃለሁ፣ ነገር ግን ባልተገነዘብሁት ሁኔታ ባጭር ጊዜ ውስጥ የነበረው ባላንስ አለቀ፣ ሁኔታው ገርሞኝ ጓደኞቸን ስጠይቅ ተመሳሳይ ችግር እንዳለባቸው ነገሩኝ። በመጨረሻም ለምን እንዲህ እንደሆነ ስንከታተል፣ ቴሌ ውስጥ የሚሰራ ጓደኛችን የዘረፋ ሚስጥሩን አጫወተን ብለዋል። በመቀጠልም፣ እኛ በተለይም በሃገር ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን እጅግ የሚያሳፍር፣ የሚያሳዝንና አሳሳቢ በሆነ ወቅት ላይ እንገኛለን። የወያኔ አገዛዝ በኛ ላይ አልፈጸመዉም የሚባል ግፍ መናገር የሚቻል አይመስለኝም። ሁሉንም ፈጽሞብናል። አሁን የምንገኘው በሞትና በህይወት መካከል ነው። እናም ወይ አይናችን እያየ መሞት እንዲሁም ልጆቻችንን እጂግ አሳዛኝ ለሆነ ጭራቅ አገዛዝ አሳልፈን መስጠት፣ ወይንም ደግሞ ከዚህ ዘረኛ አገዛዝ አፈና ለመላቀቅ በአንድነት ሆ ብለን መነሳትና ወያኔን ማስወገድ በማለት ምላሻቸውን አጠቃለዋል።

ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ የአባይ ግድብ ግንባታን ያለማንም የውጭ ሃይል እገዛ ማከናወን እቺላለሁ፣ 80 ቢሊየን ብር የሚወደኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ያዋጣል በማለት በአደባባይ ሌት ከቀን የለፈለፈ ቢሆንም፣ ያልሰበሰበውን ገንዘብ ሰብስቢያለሁ በማለት የተጋነነ ቁጥር የሚያቀርበው ዘረኛ አገዛዝ ራሱ የተናገረውና እስካሁን የሰበሰበው ገንዘብ ከሶስት ቢሊየን ብር በታች መሆኑ ለወያኔ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ።