በሠራተኛ ማኅበር የተደራጁ የኮንስትራክሽን ሠራተኞች ከሥራ ተባረርን አሉ
‹‹አውቀን ሳይሆን ነገሮች ተገጣጥመው ነው›› የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ
‹‹ድርጅቱ መፍትሔ ካላመጣ ወደ ሕግ እንሄዳለን›› የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን
ማገርኮን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ሕንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ይሠሩ የነበሩ 67 የሠራተኛ ማኅበር አባላት ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ መባረራቸውን ገለጹ፡፡