የኦሮሚያ ክልል ለ4,721 እስረኞች ፈታ
(The Reporter) — የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይቅርታ ቦርድ ለ4,721 እስረኞች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ኘሬዚዳንት አባዱላ ገመዳ በትናትናው እለት አስታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት ሕፃናት የያዙ እናቶች፣ ከ5ዐ ዓመት በላይ የሆናቸው ጐልማሶች፣ አዛውንቶችና ወጣቶች መታረማቸው በመረጋገጡ በይቅርታ እንዲፈቱ በቦርድ ተወስኗል፡፡
በክልሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ይቅርታ ያልተደረገላቸው ታራሚዎች ደግሞ በግድያ፣ በዘረፋ፣ በደን ጭፍጨፋ፣ በቀይ ሽብር፣ በሞት ፍርድ፣ በአስገድዶ መድፈር የተፈረደባቸውና ይቅርታ ተደርጐላቸው እንደገና የታሰሩና በተደጋጋሚ ወንጀል የተቀጡ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡