የዓውደ ዓመት ገበያ ድሮና ዘንድሮ

የ2002 ዓ.ም በኢድ አልፈጥር በዓል ተደምድሞ የ2003 ዓ.ም በእንቁጣጣሽ በዓል ሊጀመር በመሆኑ፣ ገበያው በተከታታይ ሁለት ቀናት በሚስተናገዱ በዓላት ምክንያት በሸማቾች ተጨናንቆ ነው የከረመው፡፡ ወትሮም በዋጋ ንረት ቁምስቅሉን የሚያየው ገበያ በዓውደ ዓመት ምክንያት እንደ እሳት መጋረፍ ጀምሯል፡፡  ድሮና ዘንድሮን በሸማቾች ተሞክሮ እያዋዛና የባለሙያን አስተያት በማካተት በዳዊት ታዬና በብርቱካን ፈንታ የተጠናከረው ልዩ ዘገባ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የታዩትን የገበያ ውጣ ውረዶች በቢዝነስ እና ኢኮኖሚ ገጽ ላይ ይመልከቱ፡፡