“በመንግሥታዊ ውንብድና ትግላችን አይገታም!” ሰማያዊ ፓርቲ
ሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን በመስቀል አደባባይ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጠራ
Ethiopia Zare (ሰኞ ነኀሴ 27 ቀን 2005 ዓ.ም. September 2, 2013)፦ እሁድ ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ የነበረው የሰማያዊ ፓርቲ ቅዳሜ ነኀሴ 25 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች መሪነት በፖሊሶች ጽሕፈት ቤቱን ጥሰው በመግባት አመራሮቹ መታሰራቸውንና ንብረቶች መወረሳቸውን ፓርቲው ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።