ኢትዮጵያውያን ያሰጋው የኮሌራ ወረርሽኝ
ምስራቅ አፍሪቃን በመታው ድርቅ የተነሳ ኢትዮጵያ ፣ ኬኒያ ጅቡቲ ሱማሊያና ዮጋንዳ የሚኖር ህዝብ አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልፅዋል። ከድርቁ ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዳይከሰቱም እየተፈራ ነው። ሮይተርስ የዜና ወኪል ባለፈው አርብ ይፋ እንዳደረገው አምስት ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኮሌራ በሽታ ሊጠቁ እንደሚችሉ አስታውቋል። ታሪክ ያሳሬቪች- የአለም የጤና ድርጅት በምህፃሩ WHO ቃል አቀባይ ናቸው- ልደት አበበ አነጋግራቸዋለች። ያዳምጡ