ይድለስ ለአቶ አበበ ገላው: ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

ዲን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል አቶ አበበ ገላው ከተባሉ ግለሰብ (የቀድሞ የኢሳት ሰራተኛ) በኢሜይል አድራሻቸው ለደረሳቸው መልዕክት የሰጡት መልስ። 

ሰላም አቶ አበበ

ስለ እኔ፣ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ ስለ ሚድያ አጠቃቀምና ስለ ዜጎች ሕጋዊ መብት ያሎት አመለካከት በቀጥታና ደረቅ መረጃ አውቅ ዘንድ ስለ ጻፉልኝ ምስጋናዬ የላቀ ነው።

በእርግጥ አንድ እርምጃ ወደ ፊት የተራመደ ሰው በቃላት ለማንኳሰስ መሞከርና ዘመቻ መክፈት በእርስዎ አልተጀመረም። ምድር እስካለች ድረስ ነፋስ አለ። ግራ አመለካከት አራማጆችና ኋላቀሮች እዚህ ምድር አስካሉ ድረስም እንዲሁ የሚያውቁት ሆነ የማያውቁትን ግለሰብ ማብጠልጠልና ማቃለል የተፈተነ አስተማማኝ መሳሪያቸው ነውና ብዕር አጣጣሎት ለእኔ እንግዳ አይደለም። አይደንቀኝምም።

በበኩሌ “የቀድሞ ስህተቴን” ላለመድገምና ከስህተቴም ለመማር ካለኝ ጽኑ ፍላጎት የተነሳ ገንቢ ሂስና ነቀፋ እንዲሁም አስተያየት የምወድና የምቀበል ግለሰብ ነኝ። የተሳሳትኩም እንደሆነ ስህተቴን በአደባባይም ቢሆን መሳሳቴን ለመግለጽና ለመቀበል የሚከብደኝ ሰው አይደለሁም። በአንጻሩ ደግሞ እርስዎን ጨምሮ ከማንም ቢሆን ስራዎቼን ተከትሎ ውዳሴ የምጠብቅ ዓይነት ሰው አለ መሆኔንም ስገልጽሎት በአክብሮት ነው። በነገራችን ላይ መማር ተገቢ መሆኑን ባምንበትም በሌላ መልኩ ግን ወደ ትምህርት ቤት የሄድኩት ምክንያት፥

  1. ከእንደዚህ ዓይነት ተራና ርካሽ ቃላቶች ራሴን ለመጠበቅ፥
  2. ሰዎች አለን በማለት የሚመኩበትን ምንም ቢሆን እንደሚቻል ለማረጋገጥ፥
  3. አደርገዋለሁ ብዬ ከተነሳሁት ዓላማም የተነሳ እንደ አሁኑ ያለ መላላጥ ሲፈጠር ደግሞ ለነገር ፈላጊዎች ክፍተት ላለመፍጠርና፥
  4. ከምንም በላይ ደግሞ የባላንጣዎቼን አፍ ለማዘጋት ነው። ደግሞም አድርጌዋለሁ።

አቶ አበበ ሙልጌታ ለማስተላለፍ ስለምትፈልገው መልዕክት የመረጃ እጥረት አለብህ ብለው የሚያምኑ ከሆነ፤ ኢሳት ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅም ስራ እየሰራ ነው ብለው የሚያኑ ከሆነ፤ እርስዎም በግልዎ በዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አምናለሁ፥ በነጻ ፕሬስ አምናለሁ፥ አንጻራዊ አመለካከት ያለው ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት ሲያንሸራሽር ማየት እወዳለሁ ከሆነ ነጥቦ (ከዚህ ቀደም ይህን ሲያደርጉ ግን አላየሁም። ይልቁንስ የተላከሎት ጽሑፍ ሲያፍኑ እንጂ) የአንድ ግለሰብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ለሀገሩ ባለው ነገር የአቅሙን ለማበርከት በሚያደርገው ትግል ለምሳሌ በስነ ጽሑፍ የተሰለፈ እንደሆነ ስራዎቹን ለንባብ/ለሕዝብ እንዳይደርሱ በማፈንና በማሳፈን ስምም በማጥፋት አላምንም ብለው የሚስቡ ከሆነ፤ ይልቁንስ ከዚህ ቀደም ሕዝብ በፖለቲካዊ አመለካከትዎ የሚያውቆት አቶ አበበ (የኢሳት ባለደረባ) መሆንዎ ቀርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር በመወያየትና በመከራከር የማምን ግለሰብ ነኝ እያሉን ያሉት እንደሆነና አዎ! የዜጎች ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አምናለሁ ብለው የሚያስቡ ከሆነ ይሄው መፍትሔው ቀላል ነው። ይኸውም፦

በአሁን ሰዓት አቶ አበበ የሚገኙበት ሁኔታ ማለትም ኢሳት ገቢ ለማሰባሰብ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች ከመሳተፍ የዘለለ ከተቋሙ ጋር ያሎት ግኑኝነት ባልውቅም ቀደም ሲሉ ግን እንደ ግለ ግዛትዎ የፈለጉትን ጠርተው የሚናግሩበት የዓይኑ ቅንድብ ያላመሮት ደግሞ ያገሉበት በነበረ ሚድያ ዜጎች በዜግነታቸው ያለመከልከልና ያለገደብ ሃሳባቸውን በነጻነት የሚገልጹበትን መድረክ አያዘጋጅተው በሚያመችዎት ሰዓት በአድራሻዬ ቢጠቁሙኝ አለሁ በማለት ድምጼን ለሰፊው ሕዝብ፥

  • ለማሰማት፣
  • ጋዜጠኝነት፤
  • ነጻ: ገለልተኛ: ፍትሐዊና ሚዛናዊ ሚድያ፤
  • ፓለቲካ፤
  • ሰብአዊነት ጎጠኝነትንና ጠባብ ዘረኝነት፤
  • ኢትዮጵያዊነት ባንዳነትና ሽብርተኝነት፤
  • እንዲሁም የሕዝብ ዓይንና ጆሮ መሆን ማለት ምን ማለት እንደሆነ ወይ ተምሬ እወጣለሁ ወይንም ደግሞ አስተምሬ አመለሳለሁ። ቀላል!

 

አውቆት ዘንድ ዕድሉ ስለ ሰጡኝ በድጋሜ አመሰግናለሁ

ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል

አፈና በዛ ጎበዝ!
ዜጎች በዜግነታቸው ሃሳባቸው በነጻነት ያለገደብ ያለመከልከልና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚስተናገዱበትና የሚያንሸራሽሩበት የነጻ ሚድያ ያለህ!

 የተሰጠው ምላሽ የአቶ አበበ ገላው መልዕክት በአድራሻቸው ለተቀበሉ ዝቅ ብለው ከታች አድራሻቸው የተዘረዘሩት ድረ ገጾች በሙሉ ተልከዋል።

Esat editor: [email protected]

addis voice: http://addisvoice.com/

addis dimts: [email protected]

ethiopiazare: [email protected]

Ecadf Ethiopia: [email protected]

EMF ethioforum: [email protected]

Ethio Sun: [email protected]

ETHIO MUNICH: [email protected]

Abugida: [email protected]

Zehabesha: [email protected]

Quatero: [email protected]

ethiomedia: [email protected]

ethiopian review: [email protected]

ethiofreedom: [email protected]