ኢትዮጵያን ሪቪው የተመሠረተበት 20ኛ ዓመት ክብረበዓል

በዚህ ዓመት አንጋፋው ኢትዮጵያን ሪቪው የተመሠረተበትን 20ኛ ዓመት በድምቀት ለማክበር በርካታ ተግባሮችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት የኢትዮጵያን ሪቪውን ያለፈውን አኩሪ ታሪክና የወደፊቱን ብሩህ ዕድል የምናሳይበት የተለያዩ ዝግጅቶችን እናቀርባለን።

ኢትዮጵያን ሪቪው ግልጽ ዓላማና ተልዕኮ አለው። በመጀመሪያና በግምባር ቀደምትነት የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርገውን ተጋድሎ የተቀደሰ ዓላማ ያለው መሆኑን ይቀበላል፣ ያከብራል። ኢትዮጵያን ሪቪው ካለፉት 20 ዓመቶች አንስንቶ ሲያደርግ እንደነበረው ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ሙሉ ድጋፉን በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥልበታል። ለወደፊቱም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዱ መረጃዎችን በማቅረብ የበኩሉን አስተዋጽኦ በትጋትና በንቃት ያበረክታል። “መረጃ ኃይል ነው!” “ህዝብ የማወቅ መብት አለው!” የሚሉ መሪ ቃሎችን አንግቦ ህዝባዊና አገራዊ አገልግሎቱን ይቀጥልበታል። የኢትዮጵያ ህዝብም ከወያኔ አፋኝ አገዛዝ የሚላቀቅበት ጊዜ ቅርብ መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያን ሪቪው ለመግለጽ ይወዳል።

እዚህ ደረጃ ልንደርስ የቻልነው በአንባቢዎቻችንና በደጋፊዎቻችን ያልተዛነፈ ፍቅርና ድጋፍ እንዲሁም በትጉህ ሰራተኞቻችን የቀንና የሌሊት ሥራ ነው።

ኢትዮጵያን ሪቪው የ 20 ዓመቶች አገልግሎት በልዩ ሥርዓት ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ ቅዳሜ July 2, 2011 (እአአ) ስለምናከብር እርስዎ እንዲገኙልን በአክብሮት ጋብዘንዎታል።

ቦታ፤ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ኤቲካል ሶሳይቲ

አድራሻ፤ 7750 16th Street NW, Washington DC 20012

የትኬት ዋጋ፤ $50 (ትኬት ከድረ ገጽ ላይ መግዛት ይቻላል። እባክዎ እዚህ ላይ ይጫኑ)


|
|

በዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ በሚካሄደው ክብረ በዓል ላይ ለመሳተፍ የማትችሉ ደጋፊዎቻችን፣ ትኬቱን በመግዛት ኢትዮጵያን ሪቪው ለወደፊቱ ላቀዳቸው ተግባሮች ማከናወኛ የሚሆን አስተዋጾ በማበርከት ተሳተፉ።