የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፖሊስ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ለውጥ አደርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፖሊስ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ለውጥ አደርጓል።

አዲሱ ሰሌዳ ይፋ የማድረግ ሥነ-ሥርዓት በነገው ዕለት በዋና መሥሪያ ቤቱ ከቀኑ 8፡00 ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፥ አዲሱ ሰሌካ ‎ከዚህ በፊት የነበረውን የተዘበራረቀና ወጥነት የሌለው የሰሌዳ አጠቃቀም ሥርዓት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው ብሏል።
‎
ሰሌዳው በፖሊስ ተሽከርካሪዎች አማካኝነት ምንም ዓይነት የዲሲፕሊን ጥሰት እንዳይፈፀም በተሟላ መልኩ ለመቆጣጠር የሚያስችል እንደሆነ ገልጿል።
‎
” ‎አዲሱ ሰሌዳ ዝም ብሎ ቀለምና ቁጥር ብቻ የተቀየረ አይደለም ” ያለው ፌዴራል ፖሊስ ” ከዘመናዊ የዲጂታል የመረጃ ቋት (Database) ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለአሠራርና ለቁጥጥር ቀላል ያደርገዋል ” ሲል አሳውቋል።

‎ከዚህም ባሻገር ሰሌዳዎቹ በህገወጥ መንገድ የማይባዙ ከፍተኛ ሰኩሪቲ ያላቸው እና የደኅንነት መጠበቂያ ምስጢራዊ መለያዎች ያሏቸው መሆኑ ለየትኛውም የማጭበርበር ስራ ተጋላጭ እንዳልሆኑ ገልጿል።
‎
አዲስ የሰሌዳ ስርዓት የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ ለመከታተል እንደሚረዳ ተመላክቷል። ይህም የወንጀል መከላከል ኦፕሬሽናል ስራዎችን በተፋጠነ፣ ፖሊሳዊ ስነምግባርን በተከተለ መንገድ መካሄዱን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ብሎም አስፈላጊ ድጋፎችን ለማድረግ ይረዳል ብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*