የኢህአዴግ የኢንቨስትመንት ጥሪ እና ዘረፋው
የኢህአዴግ የኢንቨስትመንት ጥሪ እና ዘረፋው
የኢህአዴግ ልዑካን የፊታችን ሚያዚያ 10 እና 11/2011 በአሜሪካና አውሮፓ ከተሞች በውጭ ከሚኖረው ኢትዮጵያዊ ጋር ለመምከር
እንደሚመጡ በይፋ አስታውቀዋል፤የተልእኮው ዋናው አላማው በሰሜን አፍሪካና በአረቡ ኣላም የቀጠለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ እውን
እንዲሆን ዲያስፖራው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማምከን እንዲሁም ወደሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ በስፋት እንዲፈስ ለማድረግ ያለመ ነው፤
** በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደምም በሀገር ቤት ገብተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል፤ውጤቱ ደግሞ ምን እንደነበር
ወዳጆቻችን እና ጉዋደኞቻችን በከፍተኛ ጥረት ያፈሩትን የውጭ ምንዛሪ በሰበብ አስባቡ ተዘርፈው ሕይወታቸው ሲመሳቀል ታዝበናል::
** እንኩዋን ከውጭ ሀገር የሄደው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ በሀገር ቤት በንግዱ ዓለም ዘመናት ያስቆጠሩ በሰበብ አስባብ እየተገፉ የሀገሪቱ
ኢኮኖሚ በገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች እና በጥቂት ሸሪኮቻቸው እጅ ወድቐል፤ ባለሀብቱ በግብር፣በአራጣ ወዘተ እየተሳበበ ወደ ወህኒ እየተነዳ፣
የቀረውም እየኮበለለ ይገኛል፤ጥቂት ማይባሉትም ወደ ድህነት ተገፍተዋል፤ጥቂቶችም ራሳቸውን አጥፍተዋል፤የጌታነህ ትሬዲንግ ባለቤት አቶ ዮሃንስ
ጌታነህና የአሴ ማርብል ባለቤት አቶ አስፋው ይርጋ በዚህ ረገድ ተጠቃሽ ሰለባዎች ናቸው፤
** ነጋዴው በሀገሪቱ በሰፈነው የጉልበት አገዛዝ ስጋት ውስጥ በመውደቁ የህልውናው ዋስትና አድርጎ የወሰደው በስልጣን ላይ ላሉት
ገዢዎች እጅ መንሻ ማቅረብ ነው። ስልጠን ላይ ያለው ቡድን አንድ ግዜ ለምርጫ ዘመቻ፣ሌላ ግዜ ደግሞ ለህንጻ ማሰሪያ በሚል የንግዱን
ሕብረተሰብ እያስገበረ ይገኛል፤ ኢሕአዴግ ለ2002 ምርጫ ብቻ 57 ሚሊዮን ብር ከነጋዴው ሰብስቧል፤በዚህ መልክ ነጋዴውን እያራቆተ
እስካለፈው ጥቅምት ከወጪ ቀሪ 100.3 ሚሊዮን ብር ማከማቸቱን በይፋ አስታውቐል፤
** በሀገሪቱ በሪል ስቴት መስክ ቀዳሚ የሆነው የሃያት ሪል ስቴት ባለቤትን ጨምሮ ቁጥራቸው የበዛ ነጋዴዎች በእስር ቤት ናቸው፤ለእስር
የሚሰጠው ምክንያት ታክስ፣ አራጣ የሚል ቢሆንም ፣በኩባንያዎቻቸው የገዢው መደብ ሰዎችን ባለድርሻ እንዲያደርጉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ
የሚመጣበቸውን ጥሪ ባለማስተናገድ እነደሆነም የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ሰፈር የሚነሳ ጉዳይ ነው፤
** ዲያስፖራው የግል መኖሪያ ቤት እንዲሰራ እየተጠየቀ አንዳንዶች ሄደው መስራት የ ቻሉ ቢሆንም ፣በከተማዋ ዳር ከሰሩት ውጭ
ሌሎቹ ለሰሩት ቤት ዋስትና አጥተው ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቀዋል፤ቦሌ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሎምፒያ አካባቢ ግንባታ ፈቃድ ወስደው
በቅርቡ ተሰርተው የተጠናቀቁና በመጠናቀቅ ላይ የነበሩ ዋጋቸው ከ 5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ እና የዚምቧቤ ኤምባሲን ጨምሮ የውጭ
መንግስታትና ድርጅቶች የተከራዩዋቸው .ቤቶች እንዲፈርሱ ተወስኖባቸዋል።የተወሰነባቸው። በከተማዋ ዳር የሰሩትም ቢሆኑ ከአቅም በላይ በሆነ
ምክንያት ንብረታቸውን ለመሸጥ ለመለወጥ ቢፈልጉ እንኩዋን 80 በመቶ ሰርተው ካላጠናቀቁ መሸጥ እንዳይችሉ ሕገ መንግስቱ የሰጠው የንበረት
ባለቤትነት መብት ተሽሮ በህግ ታግደዋል፤
** አቶ ስብሃት ነጋ በአደባባይ ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ተናግረው እናዳረጋገጡት ዛሬ በኢትዮጵያ ትልቁ ኩባንያ የሕወሃቱ
ኤፈርት ነው፤ርሳቸው በትግሉ ዘመን በሰበሰብነው ሀብት ተነሳን ብለው ቢናገሩም ያለምንም መያዣ 1.7 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ወስደዋል፤ወለዱ ብቻው ወደ 300 ሚሊዮን ብር ሲጠጋ ፋይሉ እንዲዘጋና እንዲጠፋ ተደርጉዋል፤የባንኩ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ገዛሀኝ ይልማ
በ1998 (በኢትዮጵያ አቆጣጠር) ራሳቸውን ያጠፉበት ን ሁኔታ የቅርብ ምንጮች ከዚህ የኤፈርት ብድር ጋር ያይዙታል፤ቀደም ሲል ከሀገሪቱ
ባንክ የወሰዱትና ያስቀሩት ገንዘብ አልበቃ ብሎአቸው ዛሬም በተጨማሪ እየወሰዱ ለፓርቲያቸው ሬዲዮ ፋና እና ለዋልታ ኢንፎርሜሽን
ማዕከል ሕንጻ ገንብተዋል፤ሌሎች በርካታ ሕንጻዎችም ደርድረዋል፤ በተከራይ በኩል ያለውን ችግር ለመቅረፍ የመንግስት ተቐማት
የነበሩበትን የመንግስት ቤት እየለቀቁ ወደ እነሱ ሕንጻዎች እንዲገቡ አድርገዋል።
** ዛሬ በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያለው ዕውነታ ከዚህም እጅግ የሰፋ በሙስና የተበከለ፤ ከሀብት እና ችሎታም ባሻገር ታማኝነትንና በይበልጥም
የደም መመዘኛን በዋናነት የሚጠይቅ በመሆኑ ሕሊናን በመሸጥ እንኩዋን የሀገር ባለድርሻ መሆን አይቻልም፤…በአጠቃላይ ሀገራችን በኢኮኖሚው መስክ ብቻ
ሳይሆን በፖለቲካውም መስክ አፈና የነገሰባት፣የሚሊዮኖች ድምጽ የታፈነባት የጨለማ ምደር ሆናለች ፤ሀገራችንን ጭለማ ውስጥ ከተው፣ሕዝብ
አደህይተው እና አራቁተው የተዘፈዘፉብንን ሸክሞች በህዝባዊ እንቅቃሴ ለመጥረግ የተላኩብንን የጭለማ መልክተኞች በማሳፈር በሀገር ቤት ላለው
ወገናችን ብርታት እንሁነው፤ ዘረኝነት ይብቃ !.አምባገነንነት ይብቃ ! ዘረፋ ይብቃ !.ድንቁርናም ይብቃ !
መልዕክታችን
መልዕክታችን ግልጽ ነው። ፍትህን መናፈቅ፤ በዘረኝነት መንገሸገሽ፤ አምባገነን አገዛዝን አምርሮ መጥላት ጥሩ ነው፤ ግን በቂ አይደለም።
በመሬት ላይ ያለውን ሃቅ የሚቀይረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ብቻ ነው። እያንዳንዳችን በተቀናጀ መንገድ ትናንሽም ብትሆን ጠጠር
ከወረወርን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክፋትን ከአገራችን ማስወገድ እንችላለ።ለራስዎ፣ ለአገርዎ እና ለወደፊቱ ትውልድ ብሩህ ራዕይ ካለዎት
እና ራዕይዎ ተሳክቶ ማየት የሚፈልጉ ከሆነ የሚከተሉትን ይፈጽሙ።
· የወያኔን የኢንቬስትመንት ግብዣ አይቀበሉ። የህዝብ መብት ባልተከበረበት፤ የህግ የበላይነት ባልሰፈነበት፤ ዘረኛነት በነገሰበት ሃገር ውስጥ
ራስዎን የገዢው ሎሌ ካላደረጉ በስተቀር በጥረትዎ ያፈሩት ንብረትባለመብት አለመሆንዎን ይወቁ። ሎሌ ከሆኑ ደግሞ ጊዜዓዊ ተጠቃሚ
እንጂ ባለመብት አይደሉም።
· ውጭ አገር የሚኖሩ ከሆነ ለቤተሰቦችዎ ገንዘብ ሲልኩ የወያኔ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ማስታገሻ በማይሆን መንገድ ያድርጉት።
ኦፊሲያላዊመንገዶችንም ሆነ ወያኔ በየአገሩ ያደራጃቸው የገንዘብ ማስተላለፊያዎችንአይጠቀሙ።
· በአገር ቤት የሚገኙትን ወገኖቻችንን መረጃ ለማስራብ ወያኔ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን አፈና ለመበጣጠስ ጥረት የሚያደረጉ
የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በገንዘብዎና በእውቀትዎ ይደግፉ::
· የተደራጀ ትግል ባነሰ ወጪና በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደርጋልና ንቅናቄያችንን ይቀላቀሉ። የእርስዎን ዝግጁነት የሚመጥኑ የአደረጃጀት
መዋቅሮችን፣ የትግል ስልቶችን እና የተሳትፎ ዓይነቶችን አዘጋጅተናል። የእርስዎን አገራዊ ራዕይ የሚያሳካ ሌላ ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ
ድርጅት ካለ ይቀላቀሉት።. ፀረ-ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶችን በገንዘብዎ፣በእውቀትዎና በጊዜዎ ይርዱ።በፀረ-ወያኔ ጎራ የተሰለፉ
ኃይሎች ተባብረው እንዲቆሙ የበኩልዎን ድርሻ ያበርክቱ። የሌሎች ድርጅቶችን ህመምና ስጋት ለመረዳት ጥረት ያድርጉ።አስታራቂ
ይሁኑ።
· ወያኔ እየሸረበልን ባለ የዘርና የሃይማኖት ቅራኔ ውስጥ እንዳንገባ፤በኢትዮጵያዊያን መካከል መግባባት እንዲሰፍን ተግተው ይስሩ።
በኢትዮጵያዊያን መካከል በዘርና ሃይማኖት ልዩነት ባለማድረግ አርዓያ ይሁኑ።
· ከአሉባልታ ነፅተው የተግባር ሰው ይሁኑ። ፓለቲካችንን ከውሸት፣ ከጭፍን ጥላቻ እና ተራ ወሬዎች ለማንፃት ተግተው ይስሩ። ከወያኔ
ድርጅቶች ጋር ፈጽሞ አይነግዱ። እቃዎቻቸውን አይግዙ፤አገልግሎቶቻቸውን አይጠቀሙ።
· በወያኔ ላይ ያለዎትን ተቃውሞ በተገኘው እድል ሁሉ ተጠቅመው ይግለፁ።ተቃውሞዎን በየበዓሉ፣ በየስብሰባው፣ በሩጫዎች፣ በሌሎች
የስፖርት ዝግጅቶች ወቅት በጩኸት፣ በፉጨት፣ በየበሩና ግርግዳው በብጥስጣሽ ወረቀቶች በመፃፍ ይግለጹ። “ሞት ለዘረኛው ወያኔ!!!
ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!!!” ይሁን መፈክርዎ።
· የህሊና እስረኞችን ይዘክሩ፤ ቤተሶቦቻቸውን ይደግፉ።ራድዮና ጋዜጣን ይከታተሉ፤ ለሌሎችም ያሰራጩ። በማናቸውም መንገድ ወያኔን
የሚጠቅም ተግባር አይፈጽሙ። በመሬት ወይም በገንዘብ አይደለሉ። መለስ እያደለ ያለው መሬት የሱ አያቶች ከጣሊያን ጋር አብረው
ሊያስወስዱት ሲጥሩ የእርስዎ አያቶች ደማቸውን አፍሰው ያሰረከቡን መሆኑን አይርሱ
· የዲፕሎማሲው ትግል አካል ይሁኑ። ሰላማዊ ሰልፍ ይውጡ፤ በረሃብአድማዎች ይሳተፉ።ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የወያኔዎችን እኩይ
ተግባራት ከማጋለጥ አይቦዝኑ።ለፓለቲከኞች፣ ለሕዝብ ተወካዮች፣ ለሥራ ባልደረቦችዎ፣ ለክፍል ጓደኞችዎዜግነትን ሳይመርጡ የወያኔን
ዘረኝነት፣ ጨፍጫፊነት፣ ዘራፊነትናአምባገነንነት ያሳውቁ።17. ጠዋት “ዛሬ ለትግሉ የማበረክተው ምንድነው?” ብለው ይጠይቁ፤
ማታጠዋት ያሉዋቸውን ፈጽመው እንደሆነ ራስዎን ይፈትሹ።ዘረኞችና አምባገነኖች ከጫኑብን ዜጋዊና ሃገራዊ ውርደት በአፋጣኝ
መገላገግል የምንችለው እነሱ ሊያዋረዱን አምረውና ተግተው እንደሚሰሩ ሁሉ እኛም አምርረንና ተግተን “አትችሉም! አንፈቅድላችሁም!”
በሚል እልህና ቁጭት በርትተን ስንሰራ ብቻ መሆኑን ፈጽሞ አይዘንጉ።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
Contact: [email protected]
ዓለም አቀፍ የሲቪክ ንቅናቄ ለለውጥ በኢትዮጵያ ሚያዚያ 2003/April 2011