“ሥራዬ ቲክቶክ ላይ የሚለጠፉ ዘግናኝ እና አሰቃቂ ቪድዮዎችን ማፅዳት ነበር”
የማኅበራዊ ሚዲያው ዓለም እጅግ ዘግናኝ እና አሰቃቂ የሚባሉ ጭንቀት የሚለቁ እንዲሁም ሕጋዊ ያልሆኑ ምሥሎች የሚለጠፉበት መድረክ ነው። ሰዎች ሲታረዱ፣ በጅምላ ሲገደሉ፣ ሕፃናት ስቃይ ሲደርስባቸው የሚያሳዩ ቪዲዮዎች እና የጥላቻ ንግግሮች . . . ይለጠፋሉ። እነዚህን ይዘቶች ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከመድረሳቸው በፊት የሚቆጣጠሩ ሰዎች አሉ።