የመለስ አገዛዝ በግንቦር ወር ሊካሄድ የታሰበውን አመጽ ፈርቷል
ግንቦት 20 ቀን 2003 ዓ.ም “የድል ቀን” አና “በቃ!” በሚሉ ስያሜዎች ኢትዮጵያውያን ለተቃውሞ አደባባይ ለመውጣት “ፌስቡክ” በተሰኘ ድረ ገጽ መረጃ እየተለዋወጡ መሆኑን ተከትሎ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰደ ነው፡፡
በተለይ በአዲስ አበባ በሚገኙ እያንዳንዱ ኢንተርኔት ቤቶች በቀበሌና በጎጥ የተደራጁ የደህንነት አባላት ቀኑን ሙሉ እንዲከታተሉ እየተደረገ ሲሆን በአንድ ጠባብ ኢንተርኔት ቤት ውስጥ እስከ ሶሶት ደህነነቶች ተመድበው በየተራ እየተፈራረቁ በመቆጣጠር ላይ እንደሚገኙ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡
የተመደቡት የደህንነት አባሎች ቀኑን ሙሉ ሲቆጣጠሩ የዋሉትን ማታ ማታ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የታዘዙ ሲሆን ሪፖርቱ በቀጥታ በአቶ በረከት ስምዖን ወደሚመራው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንደሚላክም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል በመንግስት የተያዘው አቅጣጫ የህብረተሰቡን ትኩረት በሌላ አጀንዳ ማስለወጥ ሲሆን ለዚህም ከኤርትራ ጋር ያለውን ቅሬታ እንደገና በመቀስቀስ በመንግስት ሚዲያዎች ይህ ወሬ በሰፊው እንዲናፈስ እየተደረገ ነው፡፡
ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ከሱዳን ትሪቢዩን ድህረገጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የመከላከያ በጀት ለመጨመር እቅድ መያዙን መናገራቸውም አመፁን ለማስቆም እየተደረገ ያለውን ከፍተኛ ዝግጅት እንደሚጠቁም በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እየተናገሩ ነው፡፡
በጋዜጣ ህትመት ላይ የተደረገው እስክ 50% የሚደርስ ከፍተኛ ጭማሪ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ አስተያየት ሰጪ “ህዝቡ መረጃ እንዲልብ የሚያገኝበትን ዘዴ ለማቋረጥ ፕሬሱ ራሱን በኢኮኖሚ እጥረት እንዲገድል እየተደረገ ነው፡፡” ብለዋል
ይሁን እንጂ በፌስቡክ የተጀመረው የቅስቀሳ ተግባር የቀጠለ ሲሆን እስከ አሁን ከ11 ሺህ በላይ ሠዎች እንቅስቃሴውን እንደተቀላቀሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡