ረስቼው፤ የአድራሻ ለውጥ ሳልነግርዎ!

ባለፉት ግዜያት “በወርድ ፕሬስ” ነፃ የብሎግ አድራሻ በመጠቀም እንገናኝ እንደነበረ ይታወቃል። አሁኑ ግን በአንድ ፃድቅ ቸሮታ “ዶሜን” ስለተገዛልን  www.abetokichaw.com  በሚለው ድረ ገፅ ላይ የተለመዱ ጨዋታዎቻችንን እና መረጃዎችን የምንቀባበልበት አድራሻ አበጅተናል።

ታድያ ለወትሮው በዚህች “በወርድ ፕሬስ ብሎግ” ተመዝግባችሁ በየኢሜላችሁ ስትከታተሉኝ የነበረ ወዳጆች “የት ጠፋህ?” ብላችሁ መልዕክት ሰዳችሁልኝ ባይ ግዜ አዲሱ አድራሻችንን በብሎጋችን ላይ አለመናገሬ ትዝ አለኝ! (ሞት ይርሳኝ… “ጠላትህ” እንዳይሉ ችግር የለም እኔኑ ይርሳኝ! ባይሆን “አብሮይርሳን” ማለት ነው)

አዲሳባ ያላችሁ ወዳጆች  https://www.abetokichaw.com/ በሚል ብትገቡ የሚቻላችሁ ይመስለኛል።

አብሮነታችንን ያጠንክርልን!

Filed under: Uncategorized