ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል? አቤ ቶኪቻው
ትላንት ሐምሌ 2/ 2004 ዓ.ም ታዋቂው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ኬኒያ በሚገኘው ኤርትራ ኤንባሲ መታየቱን ናይሮቢ የሚገኙ ኤርትራዊ ወዳጆቼ ነገሩኝ። ኃይሌ ገብረስላሴ ኤርትራ ኤንባሲ ምን ይሰራል!?
በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት የጭምጭምታ ወሬዎችን መናቅ አይገባም። ከዚህ በፊት ራሱ ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ ሌሎችም ራሳቸውን “ሽማግሌ” ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች ተሰባስበው በቃሊቲው እስር ቤት ሲመላለሱ ነበር። የሚል ጭምጭምታ በሰማን በማግስቱ ነው ነገሩ ሽምግልና መሆኑ የተሰማው። ማን ያውቃል አሁንም ኃይሌ ኤርትራ ኤንባሲ በታየ በነጋታው አቶ ኢሳያስ እና አቶ መለስ ሊሸማገሉ ነው የሚል ዜና እንሰማ ይሆናል።
እንግዲህ ዝርዝሩን ወደፊት የምንሰማው ቢሆንም፤ ለጊዜው ግን እኔ ነገር መደበቅ አይሆንልኝምና እንሆ ሹክ ብያችኋለሁ። ኃይሌ ገብረስላሴ በኤርትራ ኤንባሲ ትላንት ታይቶ ነበር። መቼም “የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስሎኝ ነው” አይለንም። ታድያ እንዴት እዛ ሊገኝ ቻለ?
ይቺን ያህል እኔ ወሬ ካቀበልኩ፤ እንዴት? ለምን? ከየት? ወዴት? የሚሉትን ጠለቅ ያሉትን ግምቶች ለፕሮፌሽናል ገማቾች እንተዋለን!
ኃይሌ ገብረስላሴስ የተመለከቱት ወዳጆቼ ጠርተው ሰላምታ ሰጥተውት እሱም “ታድያስ ሰላም ናችሁ” ብሎ አፀፋውን የሰጣቸው ሲሆን ከሁለት አማርኛ ተናጋሪ ሰዎች ጋ እንደነበረም ሹክ ብለውኛል!
ለ ኤርትራ ብሄራዊ ቡድን ሊሮጥ ነው
I heard he try to get investment in asmera.
ባለፈው ተከሶ ፍርድ ቤት በመቅረቡ የተነሳ ተናዶ ዜጊነት ለመለወጥ አስቦ ይሆናል እንጂ መቸም ሽምግልና እንካን አይሆንለትም፦፦፦፦፦
Haile is our icon,and the world as well! Pls let’s try to be onest to citizens like him!
በሉ ሃይሌን ለቀቅ::
Before you point at your finger at Haile, what don’t you tell us your own business with Eritrea?
እንግሊዝ አገር ኦሉምፒች ላይ ጎረበት አገር ለማሳለፍ ጉቦ ሊወሰድ ሳይሆን አይከረም