ሰዎቻችን ቋንቋቸው የተደበላለቀው ምን ተንኮል ቢያሴሩ ነው!?
አቤ ቶኪቻው
ድሮ ድሮ አሉ የሰው ልጆች ቋንቋ ሁሉ አንድ ነበር። ታድያ ከእለታት በአንዱ ቀን ትልቅ ግንብ ገንብተው ፈጣሪያቸው ያለበት ሰባተኛው ሰማይ ላይ ደርሰው ምን እያደረገ እንደሆን ሊሰልሉት አሴሩ።
የሀሳባቸውን ለመሙላትም፤ አንድም የሰው ልጅ ሳይቀር ተሰባስበው በዚህ እኩይ ስራ ላይ ተጠመዱ። እግዜርም ይህ የማይሆን የቂል ሀሳባቸው እንደማይሳካ ያውቃልና፤ በሌሎች መልካም ስራዎች ላይ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ እንዲሁም በዚህ የተነሳ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመታደግ ብሎ ይህንን ስራ ሊያቋርጥባቸው ፈለገ። ከዛም ቋንቋቸውን ደበላለቀው። ከዛስ…? ከዛማ አንዱ ብሎኬት አምጣ ሲል ውሃ ሲያቀብለው፣ ሙገር ሲሚንቶን አቀብለኝ ሲል የቀበና አሸዋ ሲያመጣ ግንቡ በየት በኩል ይግባቡ በየት በኩልስ ይገንቡ!? ሀሳባቸው ከንቱ ሆኖ ቀረ።
ይህ ታሪክ አፈታሪክ ይሁን ሀይማኖታዊ ታሪክ እንጃ፤ ግና ከድሮም ጀምሮ ስንሰማው ኖረናል። ንግግራችን እና ቋንቋችን ለመልካም ካልሆነ ቢደበላለቅ በስንት ጣዕሙ! የሚል አንኳር ሃሳብም ይዟል። እውነትም አለው።
በዛ ሰሞን “ስካይፕ እና የመሳሰሉት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂዎች በኢትዮጵያ ምድር መጠቀም ሊያስቀጣ ነው።” ተብለን፤ “አይይይ… እንግዲህማ ምን ቀረ…? ከዚህ ቀጥሎ ህልማችንንም ቁዘማችንንም ፀሎታችንንም በአዋጅ የምንቀማበት ጊዜ ደረሰ አይደለምን!?” ብለን እጅግ አድርገን ስናማርር ድንገት ከመንግስት ባለስልጣናት አንዱ ቤቴሌቪዥናችን ብቅ ብለው “ስካይፕም ሆነ ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በአዋጅ ሊከለክሉ ነው የተባለው በሬ ወለደ ወሬ ነው” ብለው ተስፋ ሰጥተውን ነበር።
በነጋታው ደግሞ ሌላው ባለስልጣን ተነስተው፤ “ስካይፕም ሆነ ሌሎች የቴሌን ገቢ የሚቀንሱ እና በደህንነት ስጋት የእኛን ኪሎ የሚቀንሱ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ጥርቅም አድርገን እንዘጋለን ምን ታመጣላችሁ!?” አይነት ንግግር መናገራቸውን ሰማን!
እኔ የምለው አቶ ሽመልስ፤ የመንግስት ቃል አቃባይ ሆነው ሳለ ለምን ቃላባይ ሲያደርጉዎት ዝም ይላሉ!? እርሶ ያቀበሉት ቃል በነጋታው “ውሸቱን ነው አትስሙት!” ሲባሉ ጎረቤትዎስ፣ ለቤተሰብዎስ፣ ለባንኮኒ ጓደኞችዎስ ምን ስም ያሰትዎታል? እንዴ ምንም ቢሆን ሁለት ፀጉር አብቀለዋልኮ… የማንም ማላገጫ ሲሆኑማ ዝም አይበሉ!? እውነቴን ነው የምልዎ እኔ ለርሶ በመቆርቆር ነው የምናገረው…! ከዚህ በኋላ፤ “ይህንን ቃል አቀብል” ሲባሉ “መጀመሪያ እውነት መሆኑን ማሉልኝና” በሉዋቸው እንጂ ዝም ብለውማ አይመኑ! እንዴነችና ስልጣኑ ባፍንጫዎ ይውጣ እንጂ የማንም መጫወቻማ አይሆኑም…!
እኔ የምለው አቶ በረከት፤ እኛማ እኮ እርሳቸውን አምነን ለስንት ወዳጆቻችን “ስካይፕ አልተከለከለም!” ብለን ነገርን መሰልዎ…!? ለወደፊቱም ቢሆን አቶ ሽመልስ የሚናገሩትን ለማረጋገጥ እርስዎ ጋር እንድንደውል ስልክዎን ቢሰጡን ደስ ይለኛል።
እዝችው ጋ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎትማ… አቶ ሽመልስ ባለፈው ጊዜ “ስካይፕ አይከለከልም” ብለው የዋሹን እለት አያይዘውም ስለ አቶ መለስ ጤና ነግረውን ነበር። “እኛ በአደባባይ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክስት ግርጥት ብለው ተመልክተናቸው እግዜር ይማራቸው እያልን እየፀለይን ነው አሁንስ ሻል አላቸው ወይ?” ብለን ብንጠይቃቸው፤ እርሳቸው ሆዬ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሙሉ ጤንነት ላይ ናቸው!” ብለው ነግረውናል። አሁን ሳስበው ግን ስካይፕ አይከለከልም ብለው እንደዋሹን ሁሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ጤና አስመልክቶ የነገሩንን ለማመን ተቸግረናል። እና እርስዎ ቢነግሩን ደስ ይለናል! አለበለዛ ግን ህዝቡ፤ የአቶ ሽመልስን ንግግር ተቃራኒ ትርጉም በመውስድ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣር ተይዘዋል በቅርቡም ቀብር ሊሆን ይችላል!” ብሎ ቢያስብ እኔ የለሁበትም።
እኔ የምለው ወዳጄ፤ ባለስልጣኖቻችን እንደምን ያለ ተንኮል አስበው ይሆን ቋንቋቸው እንዲህ የተደበላለቀባቸው!?
የተፈረደበት ሀገር እና ህዝብ
የሃገራችን ህዝብ ከተፈረደበት 20 ዓመታት አለፉ በሃገሩ ስደተኛ ሆኖ አገቱን አቀርቅሮ ዛሬን ዉሎ ነገን ለመዋል ዋስትና የሌለው በመሆኑ ሁልጊዜ በፍርሃት ወጥመድ ይኖራል ሌላው ቀርቶ በመዝናኛ ቦታዎች ሳይቀር የጌቶቹን ልሳን የሚናገር ሰው ከመጣ ሁሉም በፍርሃት ይዋጣል ጸጥታ ይሰፍናል እኔም የሄድኩት ክውጭ ነበርና ግራ ገባኝ እየቆየሁ ስሄድ እኔም ነገሩ ገባኝ ችግሩ ግን እኔ ነጻነት ሞልቶ ከተረፈበት ሃገር ነበርና የሄድኩት ለመልመድ ተቸገርኩ ሆኖም ግን መልመድ ግዴታ ነበርና እኔም ጊዜ አልወሰደብኝም ምክንያቱም ሳየው ሁሉ ነገር በታሪክ ያነበቡኩት የቀድሞ ቅኝ ገዥዎችን ባህሪ በተግባር ለማየት በመቻሌ ለቀድሞ አባቶቻችን ማለት የሀገርን ነጻነት በደማቸዉ ጠብቀው ስላቆዩን ለነሱ ያለኝ ክብር እጥፍ ድርብ ሆነ አሁን ሃገሪቱን ልማት በልማት አደረኩ እያለ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዉን ሃያ አራት ሰዓት የሚለፍው የወያኔ ጎጠኛ ቡድን ሀገሪቱን በሙሉ በራሱ ብሔር የበላይነት ቀፍዶ ይዞታል አሁን ሀገሪቱ በሙሉ ለነሱ ብቻ ነው መኖሪያ እንድትሆን የተፈቅደችው ሌላዉ ቢፈልግ ይኑር ባይፈልግ ይሙት ሀገር የሌለው ስደተኛ ሕዝብ ነው የሚሳዝን ብዙ ነገር ህያ ዓመት ሙሉ ሰምተናል ምንም አዲስ ነገር የለም ያው ነው እየሆነ ያለው የወያኔ ብሄር እና ሆድ አደሩ ጠግቦ በመንገዱ ሲተፋ ምስኪኑ ሕዝብ ግን የሚበላው አጥቶ አንጀቱ ተጣብቆ መኖር ህልም ሆኖበት ሞትን ይጠብቃል እስር ቤቶች በዚህ ምስኪን ህዝብ ሞልተዋል ከቅርብ አዋቂ ሰው እንደሰማሁት በዕሥር ቤት ውስጥ ገብቶ ያልተገረፈ ሰባዊ መብቱ ያልተነካ ብሔር-ብሔረሰብ በምንም ተአምር አይገኝም በተለይ ደግሞ ታሳሪና ተበዳይ ከሆኑት ሕዝቦች ዉስጥ
1ኛ የወለጋ አካባቢ ኦረምኛ ተናጋሪ ሕዝቦች
2ኛ የጎንደር ተወላጅ የሆኑ አማሮች በዴዴሳና በሌሎች እስር ቤቶች ሁሉ እንደሞሉ ዉስጥ አዋቂ የሆነ ካድሪ በሀዘን ነግሮኛል
3ኛ የሰሜን ሸዋ ተወላጆች የሆኑ አማሮች ሲሆኑ በተጨማሪ ይህን ወያኔዊ አሰራር የወያኔው ፓትርያርክ ቀድመው እንደሚሰሩበት ማወቅ ችያለሁ ከ1ኛ-3ኛ ያለዉን ደረጃ አወጠሁት እንጂ በቅደም ተከተል ሁሉም የችግሩ ተካፋይ ነው ሌላው አዲስ አበባ ከተማም ሆነ ሌሎች ከተሞች በሙሉ ሆቴሎች ሕንጻዎች የነወዲ መለስ ብቻ ናቸው ሃገር ቤት ያለው ወገናችን የዉጭ ዜና አይሰማም አቶ መለስ ዲስኩራቸውን ብቻ እያሰሙ በባርነት ቀንበር እየገዙ ነው የአቶ መለስና ጭፍሮቻቸው ፕላን ባርነቱን አምነን ለልጆቻቸው እንድንገዛ ነው እና እየሰሩ ያሉት በያለንበት ሁሉም ሰው እንደ አበበ ገላው በቆራጥነት መታገል አለብን ሀገሩን ሕዝቡን በመዉደድ ከሕዝብ ጋር ከቆመው ታማኙ ጀግና ከታማኝ በየነ ጋር ሆነን ልንታገል ይገባልወያኔን እንቅልፍ የነሳ ያንድነት አርማ ነዉና ትዝ ይለኛል በቅርቡ ታማኝ ደቡብ አፍሪካ ከምሄዱ በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ደሳለኝ ኃ/ ማርያም ስሙን ቀይራችሁ አንቡት እሱ በጣት የሚቆጠሩ ካድሪዎች ሰብስቦ ታማኝ እንዲህ አለ ወዘተ ሲል አይ ታማኝ እዉነተኛ ጀግና መሆኑን ነው ያረጋገጠው አቶ ኃ/ማርያም ለዘመናችን ጀግና ታማኝ በየነ
ቀድሞ በድህናው ጊዜ ትግሬዎች ለጎንደር ልዩ ፍቅር እንዳላቸው ይናገሩ ነበር ስልጣን ሲዙ የመጀመሪያ ጠላት ነው ያደርጉት ለምን ይሆን ብየ አስብ ነበር መጥየቅ ነበረብኝ እና አንድ ቲልቅ አዛዉንት የታሪክ ሰው በትዉልድ አሰመራዊ የሆኑ ቀስ ብየ ምንድ ነዉ ችግሩ ወያኔ በዚህ ህዝብ ላይ ብየ ጠየቁ ምክንያቱን ቀስ ብለው ይህ ህዝብ ሃገሩን ይወዳል ሃገር የሚወድ ህዝብ እንደት ይወዳል ወያናኧ እኮ መልኩ ነው እንጂ የኛ ስራው የባዕድ ነው አሉና ይወልቃይት ህዝብ ዛሬ በህይወት ያለ ይመስልሃል የለም በሙሉ ገለዉታል ሃገሩን ወርስዉታል ሴቶቹን ያለነሱ ካድሪ ወልቃይቴ ከሞት የተረፈ ቢኖርም ማግባት አይፈቅድለትም በሀገራችን ሰው ከሞተ ይቀበራል እንጂ አስክሬኔን አይጎተትም ሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ዉስጥ እንዲህ አይነት አረመኔዊ ስራ እይስሩ ነዉ ህዝቡን እኮ ጨርሰዉታል መሬቱን ቀምተዋል በማለት በትዝታ ብዙ ነገር አወጉኝ ይቀጥላል አሁን ለዛሬው ላጥቃለው እና እባካችሁ ልሃገራችን ለህዝባችን እንድረስለት ብሶቱን እንካፈለው ለነጻነት በሰላማዊ ትግል ለምን ተንቀሳቅስክ ተብለው ብፈላጭ ቆራጩ መለስ ለሚሰቃዩት ወገኖች እንድረስላቸው በተለይም ለጋዘጠኛ እስክንድር ነጋና ለወጣቱ ታጋይ ለአንዱአለም አራጌ ልክ ለብርቱካን ሚደቅሳ እንዳደርግነው ሁሉ ዛሬም እንታገል እንጩህላቸዉ በተረፈ ህዝባችን እባካችሁ ድረሱልን እያለ ነው ህያ አመት አወራን አይበቃም ይበቃል እንበል በቃ ይቀጥላል
የባቢሎን ግንብ ገንባታ:: አሁን ደሞ ብሀር ብሀረሰበ
How many year we took?this is the time to take action.walk like hero!