ዜናን በጨዋታ፤ የርዮት አለሙ ይግባኝ መታየት ጀመረ!
ትላንት ሰኔ 15 2004 ዓ.ም የጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ይግባኝ ታይቶ ነበር።
በይግባኟም “ከግንቦት ሰባት ጋር ወይም ከኤርትራ መንግስት ጋር አሲራለች ለሚለው ክስ ማስረጃ አልቀረበብኝም።” ብላ የተከራከረች ሲሆን ከኢትዮጵያ ሪቪው ድረ ገፅ ጋር ያላት ግንኙነት የጋዜጠኝነት ግንኙነት መሆኑን ለዚህም ክፍያ እንደተከፈላት እና ከውጪ ሀይሎች የገንዘብ ድጋፍ አግኝታለች የተባለው ይሄው የሰራችበት ክፍያ መሆኑን አስረድታለች። ያገኘችው ክፍያም አንድ ጊዜ 1500 ብር እና ሌላ ጊዜ ደግሞ 2100 የኢትዮጵያ ብር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ተናግራለች።
አቃቤ ህግ በበኩሉ ሌሎች አብረዋት የተከሰሱ ይቅርታ መጠየቃቸውን አውስቶ ርዮት አለሙ አዲሳባን ለመበጥበጥ ከውጪ ሀይሎች የገንዘብ ድጋፍ ማግኘቷን ደግሞ ለመናገር ሞክሯል።
አሽሟጣጮችም በበኩላቸው ርዮት አለሙ በድምሩ 3600 ብር አግኝታ አዲሳባን የምትበጠብጠው እንዴት ነው? ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ልጅቷ ጠጪ እንኳ ብትሆን “አንድ ምሽት በገንዘቡ ጠጥታበት በሞቅታ ከተማዋን ልትበጠብጥ ስትል በቁጥጥር ስር አውለናታል!” ለማለት ይመች ነበር። ከዚህ በላይ ግን የዘንድሮ ሶስት ሺህ ብር አይደለም ሀገር እና በሶ እንኳን መበጥበጥ ያስችላልን!? ሲሉ አሽሟጠዋል።
ለማንኛውም ቀጣዩ ቀጠሮ ለሀምሌ 10 2004 ዓ. ም ሆኗል።
real ethiopian. we need more of reeyot, a determind ethiopian. she is the kind of ethiopian who can rescue ethiopia from this termoil we are in. it is amizing to me that people ask forgivness for speaking out the truth. friends, you have every right to speak even criticism and redicule of your governement in a democratic society. a right to speak is given to every human race from God, do not let anybody take that from you.
ለነገሩ ሰርካለም ፋሲልም ነፍሰ ጡር ሆና. ሆዷ ውስጥ ጋር ካለው ህጻን ጋር እንደ ችግር ፈጣሪዎች ተፈርተው መታሰራቸው የሚገርም ብቻ ሳይሆን ያሰራቸውን አካል የአእምሮ ጤነኛነት የሚያጠራጥር ነው. በ 22/ 06 /2012 ኢሳት ባገኘው መረጃ መሰረት እንደዘገበው 546 ህጻናት ከእናቶቻቸው ጋር መታሰራቸውስ ለምን ይሆን ኢትዮጲያን እንዳይበጠብጡ ወይስ ቦንብ እንዳያጠምዱ ወይስ እስር በዘር ስለሚወረስ ለምን ኢህአዴጎች ስራ ከመጀመራቸው በፊት 24 ሰዓት ፕሮፌሽናል አገልግሎት የሚሰጣቸው ጥሩ ሜንታል ሆስፒታል እንደማይከፍቱ አልገባኝም.
አበበ, እውነትም በማስተዋል አበበ, ፍሬ ሃሳቡን ገልጸሃል,
እነ ርዮት የህዝብ ሻማ ናቸው
ጎህ እየቀደደ ነው, መለስ ወደ ወህኒ መውረጃው ቅርብ ነው