ህጋዊውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያን ይቅርታ መጠየቅ አለብን
ህጋዊውን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ይቅርታ መጠየቅ አለብን
ከተድላ ጌትነት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ ካሳለፈቻቸው ዘመናት ማለት ዘመነ ዮዲት ጉዲት ዘመነ ግራኝ ዘመነ ኢጣሊያ (የአምስቱ አመት ወረራ) የባሰ የመከራ ዘመን መግፋት ከጀመረች ድፍን 20 ዓመት ሆነ።የጉዲትም ሆነ የግራኝ ግልጽ ጠላትነት በመሆኑ አባቶቻችን የቻሉትን ቅርስና ንዋየ ቅድሳት በየዋሻውና በጉድጓድ ውስጥ በመደበቅ ጥቂት የማይባሉ ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶችንና መንፈሣዊ እሴቶችን አቆይተውልናል። በዚያ ዘመን የነበረው ግልጽ ጥፋት ለመሸሽም ሆነ ለመደበቅ ዕድል ነበረው የአሁን ዘመን የአገሬ ሰው የወዳጅ ጠላት እንደሚለው አማኝ መስለው ይልቁንም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከልና ቅርሶችንና መንፈሣዊ ሀብቶችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ ቃል ገብተው የተሾሙ በትልቁና በወሣኙ ቦታ ላይ ሆነው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋር የሚመዘብሩ አባ ጳውሎስ የቀደሞ ጠላቶች በግልጽ ሊያጠፉዋት ያልቻሉትን እርሳቸው በስውርና በግልጽ አወደሟት።
የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመንግሥት የሚቀርበው በፓትርያርኩ በኩል እንደሆነ ግልጽ ነው። ዛሬ መንግሥትን ስለ ቤተ ክርስቲያን ላይ ይህን አደረግህ ይህን አጠፋህ ማለት አይቻልም። በእርግጥ አስቀድሞ የሚስማማውን መርጦ ማስቀመጡ ባይካድም ሥርዓቱን ጠብቆ ለመንግሥት የቀረበ ጉዳይ የለም። ይህም የሆነው አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ የሌላቸው ሆኖ አይደለም አብያተ ክርስቲያናትም ችገር ሳይገጥማቸው ቀርቶ አይደለም። በተለይም የእስልምና አክራሪ ቡድኖች አብያተ ክርስቲያናትን በየጊዜው ያቃጥላሉ አሁን እየተስራፋ ያለው ሃይማኖት የለሽ ትውልድ ሥልጣን በያዘበት ቦታ ሁሉ ቀደምት የቤተ ክርስቲያናትን ይዞታና ቅርስን መንፈሣዊ እሴቶችን ሁሉ በተቻለ አቅሙ ያጠፋል። ይህን ለመከላከል የሀይማኖት መሪው ግዴታ ነበር ነገር ግን እራሱን አጥፊና አውዳሚ በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ እራሱን አጥፊ (አውዳሚ) በመሆኑ ጉዳት ደረሰ አልደረሰም ብሎ ሃይማኖቱን ወክሎ ይጮሀል ልብ በሉ የዋልድባ መታረስ የዝቁዋላ መቃጠል ለአባ ጳውሎስ ደስታ ነበር። ለዘመናት የታወቁ ለአማኙ ሕብረተሰብ ብርቅዬ የሆኑት የገዳማቱ መጻሕፍት ዘመን ተሻጋሪ ታሪካችን ሀይማኖታዊ ዕውነታዎች ባህልና ሥልጣኔን አምቀው የያዙ በታሪክ ምሁራን የእውቀት መሥራቶች ለተመራማሪዎች የጥበብ ምንጮች የሆኑ ቅርሶች ይገኙበታል ምመናን ከቦታ ደርሰው ኃጢአታቸው ይሰረይላቸዋል። ወደነዚህ ቦታዎች የደረሱ ሁሉ የመንፈስ እርካታ ያገኛሉ የለመኑትን የተሳሉትን ሁሉ ያገኙባችዋል::
በአንፃሩ ትልቅ የካውንስሊንግና የህክምና ሆስፒታሎችን ወክለው በዘመን ያልተፈታ እንቆቅልሾችን እየፈቱ ከዘመን በኋላ ላለው ተስፋም ሰንቅ ሆነው ኖረዋል። የነዚህ ገዳማት ችግር ሁሉንም ትውልድ አንቀሳቅሷል። በእግራቸው ተጉዘው እሳቱን ለማጥፋት የደከሙ በቦታው ተገኝተው እያጠፉ ልማደኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲዋሽ አይተው አትዋሽ እሳቱ አልጠፋም በማለታቸው እግራቸው በጥይት ተመተው የቆሰሉም አልጠፉም። ይህ ችግር በሀይማኖቱ መሪ አፈቀላጤዎች ውሸት ነው ተብሎ ተነገረ በአይናችን አይተን መናገር እንኳን የማንችልበት ጊዜ ላይ መሆናችን በእርግጥም እየዘነጋነው ነው እንጂ ቆይቷል ፡፡
በእርግጥ እኔ ሳስበው ግን ህጋዊው ፓትሪያሪክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቅሬዎስ ያለስማቸው ስም ሰጥተን ለቤተክርስቲያን አይጠቅሙም ብለን የተባለው ሰምተን ስናረጋግጥ እኛም ዝም አልን። አይደሉም የሚባልበት እድል በይኖርም እንኳን እውነቱን ተናግረን በሞትን ይሻለን ነበር፡፡ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የምእራባውያኑን ትራዲሽን ሳይሆን የቤተክርስቲያኒቱን ስርዓት ህግ ጠብቀው የቆዬ ግን የነበሩበት ዘመን ለመስራት የሚያስችል እድል የሌለበት በመሆኑም ስለቤተክርስቲያን መከራከር አይቻልም ነበር። ያም ሆኖ በጦርነት ቀጠናዎች እንኳን አፅናኝ አባት እየመደቡ እኛ ሐይማኖት እንጂ ፖለቲካ ምን አገባኝ እያሉ ጭንቁን ዘመን በጭንቅ አሳልፈውታል፡፡ በጦርነት የተያዙ ቦታዎች ጥለው ወደ መሀል አገር የመጡ አባቶችን ፡”ከማን ነው ተነጥላችሁ የመጣችሁት ያ እኮ ወገናችሁ፣ ልጃችሁ ነው” ብለው በማለታቸው ቂም ተቋጥሮባቸው መሀል አገሩን ወያኔ ሲቆጣጠረው ከወያኔ ቢሮ ሄደው ፓትርያሪኩ እንዲወርዱ ህዝቡ እዲያምፅ የተለያዩ ቅስቀሳዎች እንዲኖሩ ህዝቡ እንዲያምን ስልት ነደፉ። ወያኔ ውሸቱን እውነት ማድርግ የቆየ ብቸኛ እውቀቱ በመሆኑ ጊዜ ሳይወስድበት የሚባለው ሁሉ አስብሎ እንዲወርዱ ተደረገ ፡፡ ይህ ግፍ ሀሰት ሲነገር ዝም ብለን በማየታችን ቤተክርስቲን በጭንቅ የጠበቁት አባት በወሬ ሰምታችሁ ከጠላችሁ “በግልፅ ጥፋትን ታያላችሁ ዘመናችሁ የሀዘን ይሆናል” ብሎ ፈረደብን መሰል ለዘመናት አነባን። ይችን የታሪክ እውቀት የስልጣኔ አርማ የሆነችውን ቤተክርስቲን ውድቀት በዓይናችን አየን ጠላት ተሳለቀብን። ወዳጆች አፈሩብን እኛም አለቀስን። ዋልድባም ታረሰ አሰቦትም ተቃጠለ።
ይህ ሁሉ ሲሆን ህገወጡ የወያኔው አቡነ ጰውሎስ ለሽርሽር ግብፅ ነበሩ። ህጋዊው ፓትርያሪክ አቡነ መርቆሬዎስን ማንነት በአኗኗራቸውን መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማየት ይቻላል፡፡ ነጋ ከፀሎት መሸ ከፀሎት ከሚተጉ አባቶች ዋነኛ እንደሆኑ ቀርቦ ማጣራት ይቻላል፡፡ አሁን ያለው መንፈሳዊ ህይወታቸው በአንድ ቀን የመጣ አይደለም። አብሮ የኖረ ነው እንጂ ችግሩ እኛ ሳናጣራ ስለምናወራ ሳናውቅ ስለምንጣላ ነው እንጂ መንፈሳዊ ህይወት በአንድ ጀንበር የሚመጣ አይደለም። ትላንትም እንዲህ ነበሩ በእርግጥም ስለአሳዘናቸው አዝነውብናል። ሀዘናቸውም እየጎዳን ስለሆነ ይቅርታ መጠየቁ ለእኛም የህሊና እረፍት ለቤተክርስቲያን እድገት ይሰጣል። መንፈሳዊ አባታችንን ነፃ እንውጣ። እግዚአብሔርም አባ ጳውሎስን በፍርዱ ከዲያቢሎስ አገልጋዮች ጋር ይደምርልን፡፡
አሜን
ተድላ ጌትነት
ባየር፣ ጀርመን
ጸሃፊው በትክክል አስቀምጠውታል። በአቡነ መርቆሪዎስ ዘመን ቢተክርስቲያናችን ታፍራና ተከብራ እንዲሁም ገዳማት ተከብረውና አስፈላጊው ጥበቃ እየተደረገላቸው ነበር የቆዩት። አሁን ግን ነጭ ለባሹ አባ ዲያቢሎስ (ጳውሎስ)የቤተክርስቲያናችንን ዘመናዊ ዮዲት-ጉዲት ሆነውብናል። እግዚያብሔር ምሕረቱን ይስጠን።
ጸሓፊው ያሉት በሙሉ ትክክል ነው። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ላይ እኛ ምዕመናንና ካህናት ከፍተኛ በደል በድለናቸዋል። ያልሠሩትን ጥፋት እንደሠሩት አድርገን የጠላትን ርካሺ ፕሮፓጋንዳ እንደ እውነተኛ መረጃ ቆጥረን ጻድቁን እንደኃጢአተኛ ቆጥረናል። የቅዱስ አባታችንም ሃዘን ይሄው ዛሬ ‘አባ ?” ጳውሎስ የተባሉ የባዕዳን ቅጥረኛ ቤተክርስቲያኒቱን ቤተ ጥል ፣ ቤተ ክፍፍል፣ ቤተ ዘረኝነትና ቤተ መንደርተኝነት አድርገዋት ለ20 ዓመታት እየታመሰች ትገኛለች። የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ግፍ በቤተ መቅደስ ውስጥ ባህታዊ የሚገድል ”ፓትርያርክ”ሠጠን። ሐውልት አቁም አምልኩኝ የሚል ጣኦት ሠጠን። ሲኖዶስ የወሰነውን በአንዲት ሴት የሚያሺር አምባገነን ገዚ ኃይል ሠጠን። አዎ በእውነት ጸሓፊው እንዳሉት ቅዱስ አባታችንን ይቅርታ ልንጠይቃቸው ይገባል። ምክንያቱም በአባ ጳውሎስ ክፉ ሥራና በሥጋ ልጆቻቸው በነአቶ መለስ በግፍ የተሰደዱት የቅዱስ አባታችን ጻድቅነታቸው በህወተ ሥጋቸው ተመስክሯልና። ..ነገር ግን እንደ እኛ በስደት እየኖሩ በሓጥኡ በ”አባ” ጳውሎስና በሕጋዊው ቅዱስ አባታችን መካከል ልዩነት እንደለለ ሁሉ ”የሁለቱንም አመራር አንቀበልም ፣ ገለልተኞች ነን” ብለው የተቀመጡት ወገኖቻችን ሁኔታ ከሁሉም በላይ የሚያሳዝን ነው። ”ሁለቱም የእኛ አይደሉም” ይሉናል። ፓትርያርኩ መሞት ሲገባቸው መንጋውን ጥለው መምጣት አልነበረባቸውም እያሉም ለገለልተኝነታቸው ምክንያት የሚሠጡ አሉ። የሃይማኖታችን ዋና መመሪያ የሆነው ቃለ ወንጌል(የክርስቶስ ቃል)ግን የሚለው እንዲህ ነው ፣ <> ትርጉም ”ባንዲቱ ከተማ (ሀገር) መከራ ቢኣበዙባችሁ ወደ ሌላይቱ ሀገር ሸሹ። እውነት እላችሁአለሁ የሰው ልጅ (ከርስቶስ) እስኪመጣ ድረስ (ዳግም ምጽአቱ) የእስራኤልን ከተማዎች (አህጉረ ዓለምን) አትዘልቁም። ደቀ መዝሙር ከመምሕሩ ፥ አገልጋይም ከጌታው አይበልጥምና። ” ማቴ. 10 ቁጥ. 23-25. ይህም ማለት ከርስቶስ እራሱን የዚህ ዓለም ገዚዎች እንዳሳደዱት ዛሬም ቢሆን እውነተኛ የሃይማኖት መሪዎችን የዓልም ገዢዎች ማሳደዳቸው የሚጠበቅ ነው። በዚህ መሰረት ነው ቅዱስ አባታችንና ሌሎች አባቶች ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ የተገደዱት።…..እነ ምአለስ በኢትዮጵያ ውስጥ እኛ ላቆምነው ጣዖት እንጅ ከርስቶስ ማምለክ በሞት ያስቀጣል የሚል አዋጅ አዉጀው ቢሆን ኑሩ የክርስቶስን አምላክነት እየመሰከሩ መሞት ሲገባቸው ሥጋዊ ሞትን ፈርተው ሸሲተው ቢሆን ኑሮ እነዚህ ”ገለልተኛ ነን” የሚሉት ወገኖቻችን ምክንያታቸው ተገቢ ይሆን ነበር። ነገር ግን ምክንያታቸው ይህ ሳይሆን ሌላ ነው ፣ ዘመኑ ያመጣው የመንደርተኝነት በሺታ ።
ጽሁፍህ ጥሩ ነው ሁላችንንም ያስማማናል ግን ‘እግዚአብሔርም አባ ጳውሎስን በፍርዱ ከዲያቢሎስ አገልጋዮች ጋር ይደምርልን’ ብለህ የጻፍከው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችን አይወክልም:: እግዚአብሔር ያስተማረን አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብለን ለጠላቶቻችን እንድንጸልይ ነውና:: አቡነ ጳውሎስ ከማንም በላይ ለቤተክርቲያንና ለኢትዮጵያ ህልውና ጠላት ናቸው: ቢሆንም ግን ክፉን በክፉ አትቃወም ስለሚል ስራቸው ከዲያቢሎስ ስራ የከፋ ቢሆንም ከዲያቢሎስ እንዲደመሩ ግን አንመኝላቸውም::
Down diablos Gebremedhin!
አሜን ቃለ ህይወት ያስማልን ቤተክርስ አና ገዳማቶቻችንን የዳቢሎስ ግብር አስፈጽሚ ከሆኑት ከአባ ከጵውሎስ ይታደግልን
በርግጥም ከአውነት ከሆነ ጥሩ ተናግረሃል:: አወ! በሶሻሊስት ስርአት ክርስትና በሁሉም ደረጃ: ፈተና ነበር::
ዛሬ ወጣቱን በሱስ እንዲጠመድ: በሃይማኖት ያለውም እንዲከፋፈል: ማህበረ ቅዱሳን ባንድ በኩል: የሱ ተቃዋሚ በሌላ በኩል ተሰልፈው: ህዝቡን እያተራመሱት ይገኛሉ::
አሁን በቅርብ ማ. ቅዱሳን ተብየው እንዳስነበበን: ዋልድባን በቅርብ እርቀት በማለት ያሰራጩት ጽሁፍ: ጸሃፊው እንዲታመን: ስለ መንገዱ አስቸጋሪነት: መታወቂያ እየጠየቁ ስለሚያንገላቱት የወያኔ ወታደሮች ብዙ በማዉራት: እንዲሁም በገዳሙ ስለሚገኙ ታምራዊ ነገሮች በመጻፍ ጸሃፊው እንዲታምን በማድረግ: ሞኞችን ለማታለል ሞክረዋል:: ዋናው መልክታቸው ግን: ስኩዋር ፋብሪካው 60 ኪሜ ስለሚርቅ ዝም በሉ ሊሉ ሞክረዋል::
በሌላ በኩል ዲ. ሙሉጌታ ወ. ገብርኤል የተባለ የነሱ ተቃዋሚ ተብዬ :የቀረዉን ኦ. ክርስቲያን ለመያዝ: ለለነሱ እየተቸ ይጽፋል:: ክርስቲያኖች: ፈተናችን አጅግ በጥም ከባድ ነው::
የተኙት ይነቁ ዘንድ ግን አንድ ነገር ልናገር::
እዉን አቡነ መርቆርዮስ በ1984 በጠና ታመው ቢሆን ኖሮ እስከ 2004 በሰላም ይኖሩ ነበርን? ይህን ጥያቄ: ማ. ቅዱሳንም ሆነ: የ ዲ. ሙሉጌታ ደጋፊዎች: ህሊናቸዉን ሽጠዋልና: ልድገመው: ህሊናቸዉን ሽጠዋልና: ሰምተው እንዳልሰሙ ያልፉታል እንጂ: መልስ ምስጠት አይፈልጉም:: ማንኛውም በጠና የታመመ ሰው: እንዴት 20/ሃያ/ ዐመት: በሰላም ሊኖር ይችላል? ማ. ቅዱሳን የሚሰጥው መልስ ስለማያጣ: ታምር ነው ይለን ይሆናል:: በርግጥ ትክክል ቢሆኑም ዋናው ጉዳይ ግን ከዚያ በላይ ነው:: ታዲያ እንዴት ያባ ጳውሎስ እግር ሳሚ ሆናችሁሳ በሉልኝ:: ዲ. ሙሉጌታም ቢሆን: እራሱም እርኩስ መሆኑን ገና አልተረዳምና ሌላ ሊናገር አይችልም:: የሰፈነውን ዘረኝነት ሁሉም ሊዋጋ ይገባል:: ኣመሰግናለሁ::
እግዝኣብሄር ይባርክህ ይኽ ነው እውኑ ታሪክ። This is the first time i heard the truth.
Dillu Zegeye