የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩ ብቻ ከስልጣን እንዲወርዱ አይደለም የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ይወገድ ነው
ዋለልኝ መኮንን
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር ከዋሽንግተን ዲሲ በመሰብሰቢያ በአዳራሽ ውስጥ ግምባር ለግንባር በጋዜጠኛ አቶ አበበ ገላው “ነፃነት እንፈልጋለን” ቁጣ አዘል የተቃውሞ ንግግር የሳቸውን የፓርቲያቸውንና የስርአታቸውን የ21 አመት ቅጥፈትና ውንብድና ሳያስቡት በተለያዩ ድጎማዎች የስልጣን እድሜውን በሚያራዝሙለት በሀያላን ሀገሮች መንግስታት ፊት እርቃናቸውን አስቀርቶባቸው :: የነፃነት እንፈልጋለን ጥያቄ የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ፊት ለፊት በግምባር ለማሰማት ከሰማኒያ ሚሊየን በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ውስጡን እያብሰለሰለውና እያረረ መልካም አጋጣሚዎችን በመጠባበቅ ላይ ይገኝ ነበረ, ነገር ግን በአቶ አበበ ገላው ለወያኔው ለጠቅላይ ሚንስቴርና እንደተላላኪ ላገለገላቸው ለሀያላን አገሮች መንግስታት የመጀመሪያና የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በኢትዮጵያ ህዝብ ስም አስተላልፎዋል::
ህወሃት ኢሀዲግ 17 አመት ለነፃነት ታግያለው ቢልም ስልጣን ከጨበጠ የታየበት ባህሪ ግን ከነፃነት ጋር በጣም የተቃረነ ነው:: በጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርላማ 99.6 በመቶ የኢትዮጵያን ህዝብ ድጋፍ አግኝቻለው የሚለው ወያኔ ከምርጫ 97 በሁዋላ ወደፍፁም አምባገነንነት አሸጋግሮ የተለያዩ ጨቃኝና አፋኝ ህጎችን አውጥቶዋል: ሁሉንም በመንግስትና በህዝብ መካከል እንደ ድልድይ የሚያገለግሉትን የሲዚል ተቁዋማትን ህይወት አልባ አድርጎዋቸዋል ሀገራዊ ውሳኔዎች በሙሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚያስከብሩ አይደሉም በተቃራኒው የወያኔ የፓርቲ ስልጣንና የአባላቶችን ጥቅም ብቻ የሚያስከብሩ ናቸው:: ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ ጭቆናና ተላቆ ነፃነቱን ማወጅ ይፈልጋል::
ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በማን አለብኝነት ህዝብን ማሰር ማሰቃየት መግደል ግለሰቦችንና ቡድኖችን ማንቃሸሽ መሳደብ ስልጣንን ተገን አድርጎ የሀገርና የህዝብን ሀብት መዝረፍ ለግላቸው ጥቅምና ስልጣን የሀገርንና የህዝብን ጥቅም አሳልፎ መስጠትና የመሳሰሉትን ወንጀሎች ሲፈፅሙ ቆይተዋል:: ከዚህ በአቶ አበበ ገላው ከተነገራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት ጠቅላይ ሚንስትሩ ወያኔዎችና ሌሎችም የጥፋት ተባባሪዎች በአሁኑ ሰአት እራሳቸውን ፈንጂ ላይ እንደቆሙ አድርገው ሊያስቡ ይገባል እንጂ የተለያዩ ተራ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ስህተታችውን ሊደብቁ መሞከሩ አግባብ አይደለም::ምክንያቱም ስህተትን በስህተት ማከም ውጤቱ የደሀ ቀብራራ …… ….የሚባለው ተረት አይነት ይሆናል::
ልክ ከዚህ በፊት እንዳየናቸው አምባገነን አፍሪካዊያን መሪዎች በስልጣን ለመቆየትና የህዝብንና የሀገርን ሀብት ንብረት ለመዝረፍ ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ የፈፅሙዋቸውና ያስፈፅሙዋችው ኢ-ሰብአዊና ኢ-ፍታዊ ድርጊቶች: የዘር ማጥፋት: የግለሰቦችን ነብስ ማጥፋት ወንጀሎች: ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናት በከፍተኛ ሙስና የጠገቡ ባለሀብቶች መሆን: ሀገሪቱዋ እስካሁን በምግብ እራስን ለመቻል ተቀረዑ የተባሉት እስትራቴጂዎች ምንም ውጤታማ ሳይሆኑ ቀርተው በአስር ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ በከፍተኛ በርሀብ አለንጋ ከመገረፍ አለማዳናቸው: የህዝቡን ጥያቄ በአግባቡ ባለመመለሳቸው ምክንያት በመላው ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ መቀጣጠል ከአቶ አበበ ገላው የነፃነት እንፈልጋለን ቁጣ አዘል ንግግር ጋር በአንድ ላይ ተደማምረው ጠቅላይ ሚንስትሩን ወደ ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ተዘፍቀዋል:: ሰሞኑን ያየናቸው ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር በተለያዩ በአይን በሚታዩ ምልክቶች እየተገለፁ ይገኛሉ::ለምሳሌ
፨ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዋሽንግተን ዲሲ መልስ ክፉኛ ታመው ወደ አውሮፓ ለህክምና መሄዳቸው(መታመማቸውን በተለያዩ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ባቁዋቁሙዋቸው የመገናኛ ብዙሀን ባንሰማ ኖሮ የወያኔው ኢሬቴድ ለስብሰባ እንደመጡ አድርጎ ያቀርብ ነበር) :
፨ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተለመደውን ፉከራ ዛቻና ማስፈራሪያ ልክ የግል ንብረታቸው በሚመስለው ኢራቴድ ሳያሰሙ መቆየታቸው(በተለይ ከሰሜን አፍሪካ አገሮች አብዮት ወዲህ የኢትዮጵያን ህዝብ መሳደብ ቀነስ አድርገው ህዝብ ህዝብ ለመሽተት ሞክረው ነበረ ነገር ግን መሳደብ ሱስ ሆኖባቸው አርፈው መቀመጥ አልቻሉም ፊታቸውን ወደ መንግስት ባለስልጣናቶችና ካድሬዎች አዙረው ሌቦች …..ምናምን በማለት የስድብ ሱሳቸውን መወጣት ጀምረው ነበር):
፨ እንደ አንድ የኢትዮጵያን ህዝብ ማስፈራሪያ የሚጠቀሙበትን የወያኔ የ17 አመት የነፃነት ተብዬ ትግላቸውን (ለነገሩ እራሳቸውን ነፃ አውጥተዋል) የሚፎክሩበትን ግንቦት ሀያን እንካን የተለመደውን ሽለላ በአደባባይ አለማሰማታቸው(የግንቦት 20ን ቀን ወያኔ ለስልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ መሳሪያ አድርጎ እየተጠቀሙበት ይገኛል:: ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ጀግና ወያኔ ብቻ እንደሆነና የደርግን ስርአት ብቻቸውን ታግለው ከስልጣን እንዳወረዱ ለማምታታትና ለማስመሰል ይጠቀምባታል: በስልልጣን የሚፎካከሩዋቸውን ሆዳም የኦህዴድ የብአዴንና የደህዴን ካድሬዎችን የስነልቦና ጫና ለማድረግ ይጠቀሙበታል: በሁሉም ኢትዮጵያዊ ላይ የስነልቦናዊ ጫና ለማድረግ እንዴ ተራራውን ያንቀጠቀጠ ትውልድ (ለነገሩ ሰውን አንቀጠቀጥን አላሉም) አግአዚ ኦፕሬሽን ምናምን የተባሉ በፅሁፍና በፊልም መልክ አዘጋጅተው የዚህን ትውልድ አዕምሮ ለመስለብ ብዙ ደክመዋል: ወያኔን በፍፁም በጠመንጃ ማሸነፍና ከመንግስትነት ስልጣኑ ማስወገድ እንደማይቻል ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ይጠቀሙበታል የደርግን ስርአት ከስልጣን ለማውረድ የትግራይ ህዝብ ብቻ መስያትነት ስለከፈለ አሁን እያደረጉ ያለውን የሀብትና የንብረት ዘረፋ ተገቢ እንደሆነ ለማስረዳት ይጠቀሙበታል):
፨ ሙያቸውን ለሆዳቸው ሲሉ አሳልፈው በሸጡ ጋዜጠኛ ነን ባዮች የማያድን ህክምና መውሰዳቸው(ሰሞኑን ወያኔ አሉኝ የሚላቸውን ሆዳምና አይነ ደረቅ ጋዜጠኛ መሳዮች ሰብስቦ የወያኔውን መሪ ከደረሰባቸው ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር እንዲያገግሙ ለማድረግ ያልቆፈሩት ድንጋይ ያልወጡት ተራራ አልነበረም በጣም የሚገርመው የተሳሳተ መዳኒት ሰተዋቸው የባሰ ህመማቸውንና ችግራቸውን አባብሰውባቸዋል):
፨ የተለመደውን ጠቅላይ ሚንስትሩ “ቢወርዱ ማን እሳቸውን ይተካል” የሚል ይሽሙጥ ወሬ በየጫት ቤትና በየግሮሰሪው አለመብዛት:: የተለመደውን ጠቅላይ ሚንስትሩ “ቢወርዱ ማን እሳቸውን ይተካል” የሚል ይሽሙጥ ወሬ በየጫት ቤትና በየግሮሰሪው አለመብዛት በፊት በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ በየሰፈሩ እሳት የላሱ ወሬ በማራገብ ወደር የማይገኝላቸው በየከተማው በሚገኙ በጫት ቤቶችና በግሮሰሪዎች ወያኔን የሚጠሉ መስለው መረጃ መሰብሰብና ወደህዝቡ መድረስ ያለበትን መልእክት የሚያናፍሱ የወሬ ሜሲ የሆኑ ሆዳሞች ነበሩዋችው እንዚህ ወሬኞች ወያኔና ጠቅላይ ሚንስትራቸው የፖለቲካ ኪሳራ ሲገጥማቸው ከወያኔ ውጭ ለኢትዮጵያ የሚሆን መሪ እንደሌለ ይሰብኩላቸዋል በነዚህ ወሬኞች የሚናደዱት ህዝቡ ብቻ ሳይሆን የመለስ ፓርላማ ውስጥ ሌላውን ብሄር ወክለናል የሚሉትም ሆዳሞች ናቸው
፨ በደረሰባቸው የግንባር ለግንባር ተቃውሞ (ቡጢ) የወያኔና የራሱ ብቻ የሆነው ኢቲቢ የሚይዘውንና የሚጨብጠው ማጣትና::
፨ሜክሲኮ በሚካሄደው በG-20 ስብሰባ ላይ የፊት ገፅታቸው ግርጥት ማለትና ጤነኛ ያለመምሰል የመሳሰሉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ስነልቦናዊ አእምሮአዊና ፖለቲካዊ ችግር ወስጥ መሆናቸውን ያሳያል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ ጠቅላይ ሚንስትሩ ብቻ ከስልጣን እንዲወርዱ አይደለም የወያኔ አምባገነናዊና የአንድ ብሄር የስልጣንና የምጣኔ ሀብት የበላይነት ከስሩ ይወገድ ነው:: ወያኔና ጠቅላይ ሚንስትሩ በተፈጥሮአዊ ግዴታም (በህመም ወይንም በሞት) ሆነ በህዝብ አመዕ መንበረ ስልጣናቸውን መልቀቃችው አይቀርም:: ጠቅላይ ሚንስትሩ ወያኔዎችና ሌሎችም የሌብነት ተባባሪዎች ልብ ሊሉት የሚገባው በቅርብ ግዜ የህዝብን ድምፅ አፍነውና በአለም አደባባይ እራሳቸውን ህዝባቸው እንደሚወዳቸው ሲለፍፉ እንደነበሩት የሰሜን አፍሪካ መሪዎች እራሳችሁን አታታሉ:: እስካሁን እንዳየሁት እንደተፃፈው የህዝብን ጥያቄ በጉልበትና በውሸት ማፈን እንደማይቻል ነው: ወንጀላቹህና ፍርዳቹ ሳይበዛባቹ ከስልጣን አወራረዳቹ ጤናማ እንዲሆን በጥይት እያስፈራራቹህና በወሬ እየዋሻቹ የያዛችሁትን የህዝብ ስልጣን ለራሱ ለህዝቡ መልሱለት::