አበበ ባልቻ እንደ ሕወሐት? – ከተስፋዬ ገብረአብ

ከተስፋዬ ገብረአብ

“ሰው ለሰው” የተባለው ድራማ በድንገት ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። ትኩረቴን የሳበው ግን ስለ ተዋንያኑ ውክልና ፌስ ቡክ ላይ የተሰራጨው ወግ ነው። ይችን ቁራጭ መታጥፍ ለመክተብ መነሻ ሆኖኛል።

አበበ ባልቻ ሲተውነው የቆየው ገፀባህርይ (አስናቀ አሸብር) እንደ ህወሃት ወኪል ተሰይሞአል። አስናቀ በጠባዩ ለሃገሪቱ ደንታ የለውም። ገንዘብ በጣም ይወዳል። አብሮአደጉን መስፍን ሊበቀለው ይፈልጋል። ተሳዳቢ ሲሆን፣ በጉልበቱ ይመካል። በቅጥረኞቹ በኩል ሰዎችን ያስደበድባል፣ ያስገድላል። ሃብታም ካገኘ ሊዘርፈው በማሰብ ያንዣብባል። ያም ሆኖ ግን አስናቀ መጨረሻው አላማረም። ንብረት ያከማቸበትን አዳራሽ ሲከፍተው፣ በህገወጥ መንገድ ያከማቸው ንብረት ብን ብሎ ጠፍቶአል። የነበረውን ጥሬ ገንዘብ በሙሉ ወዳልታወቀ ሃብታም፣ (አላሙዲ?) በማዛወሩ በድንገት ባዶውን ቀረ። እና የደም ግፊት? አንቀጥቅጦ ገደለው። የቅርብ ረዳቱ እያሳቀበት ህይወቱ አለፈች።

መስፍን የተባለው ገፀባህርይ በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ተመስሎአል። ማህሌት ደግሞ የኢትዮጵያ ምሳሌ ነበረች። የመስፍንና የማህሌት ሁለት ልጆች የኢትዮጵያ ህዝብ ወኪሎች ኖረዋል። ሴቷ ልጅ ውጭ ሃገር በስደት ላይ፣ ወንዱ ደግሞ (ብሩክ) በአገር ቤት ይኖራሉ። ውጭ ሃገር ያለችው ሴት ልጅ በዚያው ቀልጣ ቀርታለች። ብሩክ የፍቅረኛውንና የልጁን ህይወት ለማዳን መከራውን ያያል። መስፍን በባህርይው ህገወጥ ነገር አይወድም። ለሃገሩ በጎ ነገር ይመኛል። ሚዛናዊ ነው። እልኸኛ ሲሆን፣ ፈሪ አይደለም። ቤተሰቡን ይወዳል። የፕሮፌሰር መስፍንን ሰብእና ለመቅረፅ የታሰበ ይመስላል።

የወያኔ ድርጅታዊ አሰራሮች በድራማው በብዙ ቦታ ተጋልጠዋል። ለአብነት ማህሌት ህገወጥ ተግባር እንድትፈፅም ያደረጋት ራሱ አስናቀ ነበር። መልሶ ግን ማስረጃውን ለግል ጥቅሙ በማዋል ማህሌት እንድትንበረከክለት ለማድረግ ሲሞክር ይታያል። ወያኔ እነ አባዱላን ወንጀል እንዲሰሩ ካደረገ በሁዋላ መልሶ እንደፈለገ የሚጠቀምባቸው በዚሁ መንገድ ነበር። እንደ ማህሌት በየዋህነት የፈፀሙት ወንጀል እንዳይጋለጥባቸው ሲሉ፣ ለህወሃት እየሰገዱ ለመኖር የተገደዱ በርካታ ባለስልጣናትን አውቃለሁ።

ልኡል (የአስናቀ ወንድ ልጅ) ከህወሃት የተወገዱት የህወሃት አመራር አባላት ወኪል ነው ተብሏል። ልኡል የህወሃት ወኪል ልጅ ቢሆንም፣ የስርአቱን ህገወጥ ድርጊት በመቃወም ወደ ሰፊው ህዝብ ጎራ ተቀላቅሎአል። የልኡልና የመስፍን ውይይቶች በጠቅላላ የህወሃትን አካሄድ በሚቃወሙ የህወሃት አባላትና በተቃዋሚ ሃይላት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲጠቁም ተደርጎ ተቀርፆአል። በርግጥ ደራስያኑ ይህን ስለማሰባቸው የሚታወቅ ነገር የለም። የተደራስያን መብት የሚባል ነገር ግን አለ። በተለይ አፈና ባለበት ስርአት ውስጥ የሚኖር ተደራሲ ማንኛውንም የጥበብ ስራ ከወቅታዊ አስተሳሰቦች ጋር ለማመሳሰል ጥረት ማድረጉ የተለመደ ነው።

የገፀባህርያቱ ዝርዝር ውክልና ሳያስገርመኝ አልቀረም። መለስ ብዬ ታሪኩን አንድ ባንድ ሳሰላስለው በትክክልም አሁን ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ፍንትው አድርጎ ሲገልፅ የሰነበተ ድራማ ይመስላል። ድራማው በፍጥነት እንዲቋጭ የተደረገው ፖለቲካዊ ይዘት እንዳለው በመታወቁ ይሆን?

በኔ የግል አስተያየት ድራማው በጥሩ አጨራረስ ተደምድሞአል። ያልተስማማኝ ጉዳይ ቢኖር መዲ ከነልጇ መሞቷ ነው። ፅንስ ሁልጊዜ፣ ከትውልድ መቀጠልና ከተስፋ ጋር የሚዛመድ እንደመሆኑ፣ ክስተቱ ተስፋን የሚገድል ሆኖብኛል። ማህሌት እንደ ኢትዮጵያ ወኪልነቷ የልጅ ልጇን ማየት ነበረባት። በእርግጥ ድራማው ያለቀው ብሩክ ከመሰደዱ በፊት መሆኑ የድራማው ጠንካራ ጎን ነው። ድራማው ከማለቁ በፊት ብሩክ በቁጣ ወደ ፍቅረኛው እናት ሲራመድ አይተናል። ይህ የብሩክ እንቅስቃሴ ህዝብ ሲቆጣ ሊፈፅም የሚችለውን የመጨረሻ አደገኛ ሁኔታ የሚጠቁም ሆኖ ታይቶአል። የመድሃኒት እናት ልጇን የገደለችው ባለማወቅ ነው። ይህች ሴት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ወኪል ትመስላለች። ባለማወቅ የራስ ጥቅም ላይ ጥይት መተኮስ።

ድራማው ያላለቀ ቢመስልም በጥሩ ሁኔታ ተደምድሞአል። ርግጥ ነው ሟቾች በዝተዋል። በለውጥ ወቅት መስዋእትነት የሚጠበቅ ነው። ተወዳጁ ገፀባህርይ መስፍን በመጨረሻ ድል ማድረጉ ተስፋ ነው። የኢትዮጵያ ተምሳሌት ሆና የሰነበተችው ማህሌት በጭንቀትና በፍርሃት እንደተዋጠች ድራማው ማለቁ በትክክልም አሁን ኢትዮጵያ ያለችበትን አስጨናቂ ሁኔታ ይጠቁማል። የአስናቀ አወዳደቅ የህወሃትን የመጪው ዘመን እጣ ፈንታ ያመላክታል።

በረከትና መለስ ድራማው ገብቶአቸው ከሆነ ብዙ ሊማሩበት ይችላሉ። ኢህአዴግ 99.6 % በመቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ደጋፊዬ ነው እያለ የራሱን ድምፅ ይሰማል። ከእለታት አንድ ቀን አዳራሹን ሲከፍቱት ግን ባዶ ሆኖ ያገኘዋል። በመጨረሻ ደራስያኑን አድንቄያለሁ። በመቀጠል መሪ ተዋንያኑ ሊመሰገኑ ይገባቸዋል። ዳይሬክተሩና የድምፅ ባለሞያው፣ ወደር የላቸውም። የጥበብ አምላክ ሌላ ብዙ ያፈልቁ ዘንድ ያግዛቸው።

16 Comments on “አበበ ባልቻ እንደ ሕወሐት? – ከተስፋዬ ገብረአብ”

  1. አቢት ተስፋየ የማታመታው ጉድ መችም የለም በርውነትም በትክክል ፈልሙ ያገሪቱን ሁኒታ ያሳይል ያሚገርመው ነገር ግን አንድም ቀን አሰቢው አላውቀም በል እንግዲህ ገመና ማንን እንድሚቱቁም ደግሞ ንገረን እናመሰግናለን

  2. Ohh Tesfish
    The drama is still on…they r gonna take a break and will come back most likely after Euro Soccer
    That was the second season was the drama. So alalekem new yemilih..

    Wukilinaw ejig geremegn…What a mind! papapapap
    Please go to the comments after the drama on diretube , you will laugh a lot with the comments there

    hahahahah

  3. Tesfish,

    Thank you and God bless you. You are far-sighted as always! I was laughing the whole day in my work place while I remind your perfect analysis. Please keep it up!

  4. ድራማ ውስጥ ዘፈን ወስጥ ፖለቲካ አለ እያላችሁ ነገር ቆፍሩ ኢትዮጵያ ያለ ሰው ለዚህ ግዜ የለውም ስራ ፈት ሁላ::
    ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ እንዳሉት እናንተም ስራ ከምፈታ ነገር ልቆፍር ብላችሁዋል:: ላይፍ ቦሪንግ ሲሆን በፖለቲካ ማጣፈጥ አይቻልም::

  5. The writer of this article has a very sick mind. He tried to correleate things and persons which can NOT be correlated. This is called Allegory!! How on earth Asnake is correlated to EPRDF?? Mesfin and Mahlet to Ethiopia? And others?? The drama did not have any political message. It was all about how people can be dangerous to others and how people can also be solutions for others. It may also have some sociological significance. But there has no even an infinitesmal relevance with politics. It is only if you have a very sick and weak mind that you may accept this article. I found the article foolish, silly and immature. If I were the writer, I would probably spend most of my time in reading, not writing. Let me say it again, the drama has NO political implication. It was an entertaining drama which is full of social values. No politics in the drama!!!

    • Good observation Tazabi. Tesfaye (Tesfay) had an episode of schizophrenia while he was an adolescent. He has clearly wrote about that in his previous book (yegazetegnaw mastawesha). The disease has high chance of persistence or recurrence.

  6. BRAVO TESFAYE !!!
    I like the way you describe this wonderful show. you are brilliant. I am not sure if Melese and
    Bereket understand the story. Do you think they get it? I don’t think so.

  7. It is very unfortunate that Fascist Meles will not learn from others or even from his own mistakes because he is blinded by greed and power. His hatred for Ethiopia and Ethiopians is cancereous which will end up in his demise. I hope geniune Ethriopians from Tigrai dissociate from this fascist whose main goal is prolonging his reign of terror.

  8. አይ ተስፋዬ – በአይነ -ሥውራንና በፓለቲከኞች ያለው ልዪነት እኮ አንድ ብቻ ነው። በውን ዓይናቸው የታወረው በአእምሮአቸው ያያሉ ያነባሉ። ፓለቲከኞች ግን አይናቸውም አእምሮአቸውም የታወረ ነው። ወያኔ ራሱን እያታለለ ህዝብ ይወደኛል ማለቱ በራስ እንደ መቀለድ ነው።

  9. ድሮ “ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ ነበር” አሁን ደግሞ “ጅብ በሚታወቅበት አገር ቆርበት አንጥፉልኝ” ሆኖል፡፡አይደል ተስፋቢስ! ጠባብ ዘረኛ፡፡ ከአመታት በፊት በፃፍሀው መጻፍ ብዙዎቻችን ብዙ ሆነናል ዛሬ ደግሞ ስለፍትህ ስለመልካም አስተዳደር ትደሰኩራለህ

    • ኣየ አራዳ አርአያ አንተ አስከ መቼ ነህ በኤትዮጵያ አንጡራ ይምትነረው?አይጝ ኣይጝ አልዳነበረ አስጠግጝ ነዋ.ከኤርትራና ኤትዮፕያ ተጣልተ ደም አፍስሰህ ማስጌቢይው የሌለው እንስት ሆናሀል.ትናንትና ስምህ ቀይርህ ቃንቃህ ቀይረህ እንደነበርክ ጌዜው ሞተዋል እና ነጋ መስጠጌህ ፈለግ

  10. ተሰፋየ ይህንን በማለትህ ለራስህ ርካታ ቢሆንም በስላም ደስ ብሎን የምናየውን ድራማ በነበረከት ቁጣ ሊላ ነገር እንዳያመጡ እሰጋለሁ:: እረፍት የሊለው አይምሮ ነው ያለሀ አቦ! ተንኮለኛ!

  11. ኣቶ ተስፋዪ ግሩም አገላለስ ነው ትልቅ ትምህርት ነው ስለትያትሩ የሰጠሐው በርታ::ኢትዮጵያን እግዚአብሒር ይጠብቃታል ::ሀያሉ ልኡል እግዚአብሒር ሐቀኛ የኢትዮጵያን ልጆች ይጠብቅ::ድል ለኢትዮጵያ ሞትና ውርደት ለሊባው መለስና ለጭፍሮቹ::እናሽንፋለን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*