የተከበሩ የወያኔ ጠቅላይ ምንስቴር የህችን ደብዳቤ በደንብ ለሚሰድቡትና ለሚያዋርዱት ፓርላማዎት ያንብቡላቸው
ዋለልኝ መኮንን
የተከበሩ የወያኔ ጠቅላይ ምንስቴር የህችን ደብዳቤ በደንብ ለሚሰድቡትና ለሚያዋርዱት ፓርላማዎት ያንብቡላቸው
ላለፉት 21 አመታት የእርሶንና የሎሌዎቾን የውንብድና የህዝብና የሀገር ሀብት ዘረፋ እድሜ ለማራዘም እያሉ ኢትዮጵያዊያንን በተለያዩ ምክንያቶች በመከፋፈልና እርስ በእርሳቸው በማበጣበጥ ሁሉም ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች በዲምክራሲያዊ ስርአት ባልው መልኩ ወደ ህዝባዊ ስልጣን እንዳይመጡ ከህዝብ የተዘረፈውን ሀብቶንና ጉልበትዎን ሲያጠፉ ከርመዋል። እስካሁን እርሶና ሎሌዎችዎ በጋራ የፈጠሩዋችው ህዝብን በብሄር: በሀይማኖት: በቋንቋ: በጎጥ: በአናናር ዘይቤው: ከቀድሞ ስርአቶች ጋር በነበራቸው ትስስር ወዘተ መከፋፈልን በመፍጠርና እነዚህም ዘዴዎችዎ ጉልበትዎንና ገንዘብዎን ተጠቅመው ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙ አድርገው ወያኔ ስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ብቻ ኢትዮጵያና ህዝቦቻ በሰላም የሚኖሩ እስኪ መስለን ድረስ አጭበርብራችሁናል ።
እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሳችሁበትን ግፍና በደል ሳያንስ የእርስዎ በተደጋጋሚ በሲቃ የሚናገሩት ስልጣኔን እለቃለው ውሸት አዘል ጩኸት ህብረተሰቡን አሁን ካቀጣጠለው ሁሉንም አቀፍ (ሰላማዊና ኢ-ሰላማዊ) የሆነ የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ካልሆነ በስተቀር ላለፉ ሀያ አንድ አመታት ያየነውና የተገነዘብነው ግብርዎ የግል ባህሪዎ ለህግ የበላይነትን ለማስፈን ያለዎት ቁርጠኝነት ያመጡት ሰላም ብልፅግና ዲሞክራሲ የመፃፍ የመናገር በአደባባይ ተቃውሞ ማካሄድ የመሰብሰብ መብቶችን ባጠቃላይ ለመልካም አስተዳደርና ለዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እንደግብአት የሚጠቅሙትን የመገናኛ ብዙሀን መስፋፋት የተቃዋሚ ታርቲዎች መጎልበት የህዝብ በማህበራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ሶስቱ የስልጣን አካላት ከፓርቲ እጅ ንክኪ ነፃ መሆን በነዚ ሁሉ መመዘኛዎች ጠቅላይ ሚንስቴሩና ፓርቲያቸው ሲፈተሹ ምንም ሚዛን የሚደፋ ስራዎች አልሰሩም ወይንም ሆን ብለው ለመስራት አልፈለጉም::
የወያኔ ጠቅላይ ሚንስትሩ የዛቻና የስድብ ሰለባ የሆኑትና ከገዚው የትግሬ ቡድንም ሆነ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋርም ጭምር ሆድና ጀርባ የሆኑት የኢሀዲግ ፓርላማ ውስጥ የሚገኙት የሌሎች ብሄር ተወካይ ነን ባዮች ላይ በተደጋጋሚ በመለስ ዜናዊ የተለያየ አፅያፊ ስድብ ስም ፍረጃ ሲደርስባቸው ከርመዋል:: በጣም የሚያሳፍረው እነዚህ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ለባርነት ለስደት ለችግር ለፍትህ እጦት ለሀብት ንብረት አገር መሬት አልባ እንዲሆን አሳልፈው ለተራቡ ለጅቦች የሰጡ ስለ ወከላቸው ህዝብ አንገታቸውን ቀና አድርገው አንድም ቀን ሳይናገሩ ሁለት አስርት አመታትን አሳለፉ:: በዚሁ የህዝብ ውክልና እድሜያቸው በአንድ በኩል የኢትዮጵያን ህዝብ ቆመው ሲያዘርፉና ሲዘርፉ በሌላው በኩል የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ሆነው የመረጣቸውን ህዝብ በማፈንና በማሰቃየትና በማወናበድ ህዝቡ ጠላቱ ወያኔ መሆኑን እንዳያውቅና የተባበረ ክንዱን እንዳያሳርፍበት አድርገውታል::
የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትሩም እነዚሁን የህዝብ ተወካዮች ተብዬዎችን በኢሐዲግ ፓርላማቸው በተደጋጋሚ ከፍ ዝቅ አድርገው እየሰደቡ ለኢትዮጵያ ህዝብ “አናንተን የበደሉዋችሁ የወከላችሁዋቸው ግለሰቦች ናቸው” ብለው ለመቀላመድ ሲሞክሩ ተስተውለዋል:: የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴርና አጋፋሪዎቻችው የጭቡ ፓርላማቸውን የመሰረቱበት አላማ አንደኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ ስርአት አለን ብለው ከእርዳታ ለጋሽ ሀገራት ብዙ ዶላር ለማግኝት ሲሆን ሁለተኛው የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትሩ ህዝቡን የሚያስፈራሩበትና በተወካይ ተብዬዎቹ ላይ የራሱን ወገኖች እንደጠላት እንዲቆጥራቸው መቀስቀሻ መድረክ እስኪመስል ሆኖዋል:: የኢትዮጵያ ህዝብ የወያኔውን ጠቅላይ ሚንስትር እንደ አሳ ሙልጭ ሙልጭ የሚሉትን ባህሪያቸውን ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ስድባቸውን ከመጤፍ አልቆጠረውም:: ምክንያቱም ላለፉት ሁለት አስርት አመታት በህዝቡ ላይ ለደረሰው የህይወት ምስቅልቅል የዘር መጥፋትና መፅዳት የሀብት የንብረትና መሬት ዘረፋ ዋነኛው ተጠያቂዎች የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴሩ: በዘር የተንዘራዘሩዋቸው: ጦርነት የወለዳቸው ሌቦችና ወክለናችሁዋል ያሉት ለግል ጥቅማቸው ህዝባቸውን አሳልፈው የሸጡትም መሆናቸውን ጠንቅቆ ይረዳል::
ክቡር የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር እስካሁን በቆዩበት የስልጣን ዕድሜዎት ትልልቅ ሹም ሽሮችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ነገር ግን እስካሁን ያካሄዱት ሹም ሽሮች የኢትዮጵያን ህዝብ መብትና ጥቅም ያስከበሩ አይደሉም:: በተቃራኒው የራሶትን: ለብዙ ዘርዎን ለተንዘራዘሩ: ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ህዝባቸውን አሳልፈው ለባርነት ለሸጡና: በሙስና ለተወዳጁዋቸው ባዕዳኖች ጥቅም ያስከበሩ ናቸው:: በተጨማሪም እስካሁን ያደረጉዋቸው ሹም ሽሮች የተፈለገውን የህግ የበላይነትን ማስፈን: የፍትህ ማጣት: የተንሰራፋ የሀብትና ንብረት ዘረፋ: እርሀብና የተለያዩ የህይወት ምስቅልቅሎችን ማስወገድ አልቻለም:: ስለዚህ ክቡር የወያኔው ጠቅላይ ሚንስቴር የእስከዛሬው ሹም ሽርዎ ጉልቻ ቢለዋወጥ….. ስለሆነ የቀረዎት አንድና አንድ አማራጭ እራስዎንና ፓርቲዎትን ከስልጣን መሻር ነው ካልሆነ ግን ልክ እንደ ሰሜን አፍሪካ መሪዎች መጨረሻችሁ ያላማረ እንዳይሆን እፈራለው::